Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 29:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ ‘የግብጽን ምድር ለንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ለሠራዊቱ እንደ ደመወዝ ይሆንለት ዘንድ በዘረፋና በብዝበዛ የሚያገኘውን ሀብት ሁሉ ይዞ ይሄዳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ግብጽን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጣለሁ፤ ሀብቷን ሁሉ ያግዛል፤ ለሰራዊቱም ደመወዝ ይሆን ዘንድ ምድሪቱን ይበዘብዛል፤ ይመዘብራልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፤ ብዛትዋን ያነሳል፥ ምርኮዋን ይማርካል፥ ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፥ ብዛትዋንም ይወስዳል ምርኮዋንም ይማርካል ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፥ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 29:19
12 交叉引用  

እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ንጉሥ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እዚያው በባሕር መካከል አጥማጆች መረባቸውን ለማድረቅ የሚያሰጡበት ስፍራ አደርጋታለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ሕዝቦች ጢሮስን ይመዘብራሉ።


በደቡባዊ ግብጽ ጳጥሮስ የተባለውን ከተማ ባድማ አደርጋለሁ፤ በሰሜን በኩል በምትገኘው በጾዓን ከተማ ላይም እሳት አቀጣጥላለሁ፤ የቴብስንም ከተማ በፍርድ እቀጣለሁ።


በግብጽ ጦርነት ይሆናል፤ በኢትዮጵያም አስጨናቂ ሁከት ይደርሳል፤ ብዙዎች በግብጽ ምድር ይገደላሉ፤ አገሪቱም ተመዝብራ መሠረቶችዋ ይናጋሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥና ብዛት ላለው ሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገር፥ ‘በታላቅነት ከማን ጋር ትመሳሰላለህ?


ልዑል እግዚአብሔር ለግብጽ ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።


እኔ ግብጽን ወና እና ባድማ በማደርግበትና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ በማጠፋበት ጊዜ፥ አንተና ሕዝብህ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ፤


ከሕዝቦች መካከል የተመለሱትም ሰዎች በምድር እምብርት ላይ ይኖራሉ፤ እነርሱም እንስሶችና ቈሳቊስ አሉአቸው። ባድማ የነበረችውም ምድር አሁን የሰው መኖሪያ ሆናለች፤ ሐሳቤ ምርኮን ለመማረክና ለመውሰድ፥ እንዲሁም በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ነው።


跟着我们:

广告


广告