Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በርሷ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ፤ በመንገዶቿ ላይ ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ ከየአቅጣጫው በሚመጣ ሰይፍ፣ የታረዱት በውስጧ ይወድቃሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ቸነ​ፈ​ር​ንም በአ​ንቺ ላይ፥ ደም​ንም በጎ​ዳ​ናሽ ላይ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ከዙ​ሪ​ያ​ሽም በላ​ይሽ ባለ ሰይፍ የተ​ወጉ በመ​ካ​ከ​ልሽ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ቸነፈርንም በእርስዋ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፥ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:23
13 交叉引用  

‘ታዲያ ወዴት እንሂድ?’ ብለው ቢጠይቁህ፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬ የነገርኳቸውን አስታውሳቸው፤ ‘በመቅሠፍት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በመቅሠፍት ይሞታሉ! በጦርነት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በጦርነት ይሞታሉ! በራብ እንዲሞቱ የተፈረደባቸውም በራብ ይሞታሉ። ተማርከው እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ወደ ምርኮ ይሂዱ።’


እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤


“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በቊጣ አማታው፤ ሰይፉም በመደጋገም ተወዛውዞ እየዞረም የሚገድል፥ የሚያሸብርና የሚያርድ ሰይፍ ነው፤


አንተ ስለታም ሰይፍ! ስለትህ በዞረበት በቀኝና በግራ ቈራርጥ!


እኔ ሞአብን እቀጣለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


በቊጣ ከተመላ ቅጣቴ ጋር ታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በእነርሱም ላይ በምወስደው እርምጃ እኔ እግዚአብሔር መሆን ያውቃሉ።’ ”


ይህንንም በማድረጋችሁ ኀይሌን እገልጥላችኋለሁ፤ በምርኮኛነት ለሕዝቦች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ዳግመኛ በሕዝብነት የማትታወቁ እስክትሆኑ ድረስ ጨርሼ አጠፋችኋለሁ፤ ከዚያ በኋላ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ”


በግብጽ ጦርነት ይሆናል፤ በኢትዮጵያም አስጨናቂ ሁከት ይደርሳል፤ ብዙዎች በግብጽ ምድር ይገደላሉ፤ አገሪቱም ተመዝብራ መሠረቶችዋ ይናጋሉ።


“የሰሜን መሳፍንትና ሲዶናውያን እዚያ ናቸው፤ በሥልጣናቸው ተመክተው ሽብር ቢነዙም እንኳ ከተገደሉት ጋር በውርደት ወደ ሙታን ዓለም ወርደዋል፤ በሰይፍ ተገድለው ኀፍረታቸውን በመከናነብ ከወረዱት ጋር በእግዚአብሔር ሳያምኑ ተጋድመዋል።


በቸነፈርና በግድያ እንዲቀጣ እፈርድበታለሁ፤ በእርሱ ላይ፥ በወታደሮቹ ላይና ከእርሱ ጋር በነበሩት ሰዎች ላይ የዝናብ ዶፍ፥ የበረዶ ናዳ፥ እሳትና ዲን አዘንብባቸዋለሁ።


ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።


ራብንና የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይገድላሉ፤ ጦርነትንም አመጣባችኋለሁ፤ መቅሠፍትና ግድያም በመካከላችሁ ይስፋፋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


跟着我们:

广告


广告