Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነሆ ጠፋህ! ለዘለዓለምም አትገኝም፤ ያውቁህ የነበሩ አገሮች ሁሉ ተሸብረዋል፤ በአንተ ላይ የደረሰው መጥፎ ዕድል እንዳይገጥማቸውም ፈርተዋል።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሚያውቁህን አሕዛብ ሁሉ፣ ሁኔታህ አስደንግጧቸዋል፤ መጨረሻህ የሚያሳዝን ሆነ፤ ከእንግዲህ ህልውና የለህም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፤ አንተ ለድንጋጤ ሆነሃል፥ እስከ ዘለዓለምም አትገኝም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ሕ​ዛ​ብም ውስጥ የሚ​ያ​ው​ቁህ ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ አን​ተም ለድ​ን​ጋጤ ሆነ​ሃል፤ እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም አት​ኖ​ርም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፥ አንተ ለድንጋጤ ሆነሃል፥ እስከ ዘላለምም አትገኝም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:19
12 交叉引用  

ትዕቢተኞች የሆኑትን መሳፍንት ያዋርዳል፤ ታላላቅ ነገሥታትንም ያርበደብዳል።


ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን የሚያሰጡበት አለት ብቻ አግጥጦ ይቀራል፤ ከተማይቱ ዳግመኛ አትታደስም፤ ይህም የሚሆነው እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ ተናገርኩ ነው።”


መጨረሻሽ አስፈሪ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍጻሜሽ ይሆናል፤ ሰዎች ቢፈልጉሽ እንኳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቶ አያገኙሽም፤” እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


ከዓለም ሕዝቦች በጣም ጨካኞች በሆኑት በኀያላን ሰይፍ፥ ብዛት ያለው ሕዝብህ ይወድቃል፤ እነርሱም የግብጽን ትዕቢት ያዋርዳሉ፤ ብዛት ያለው ሕዝብዋም ይጠፋል።


“በማታውቃቸው ሕዝቦች መካከል የጥፋትህን ዜና በማሰማበት ጊዜ የብዙ ሕዝቦችን ልብ አስጨንቃለሁ።


ከዚህ በኋላ አንድ ብርቱ መልአክ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚያኽል አንድ ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በኀይል ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አትገኝም፤


跟着我们:

广告


广告