Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 መልከ ቀና በመሆንህ እጅግ ታብየህ ነበር፤ ክብር በመፈለግህም ጥበብን አቃለልክ፤ ከዚህም የተነሣ አምዘግዝጌ ወደ መሬት ጣልኩህ፤ ለሌሎች ነገሥታትም የመቀጣጫ ምልክት አደረግሁህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በው​በ​ትህ ምክ​ን​ያት ልብህ ኰር​ቶ​አል፤ ከክ​ብ​ርህ የተ​ነሣ ጥበ​ብ​ህን አረ​ከ​ስህ፤ በም​ድር ላይ ጣል​ሁህ፤ ያዩ​ህም፥ ይዘ​ብ​ቱ​ብ​ህም ዘንድ በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት አሳ​ልፌ ሰጠ​ሁህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፥ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፥ በምድር ላይ ጣልሁህ ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት ሰጠሁህ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:17
28 交叉引用  

ትሑታንን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን በምድር ላይ ጥሎ ያዋርዳቸዋል።


በሚያዳልጥ ስፍራ ታኖራቸዋለህ፤ ወድቀው እንዲጠፉም ታደርጋቸዋለህ።


ትዕቢት ውርደትን ያስከትላል፤ ትሕትና ግን ጥበብን ያስገኛል።


ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል።


የሞአብን ምሽጎች ከታላላቅ ግንቦቻቸው ጋር ያፈራርሳል፤ ተሰባብረውም ከትቢያ ጋር ይቀላቀላሉ።


በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል። አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል።


ጥበበኞቻችሁ ኀፍረት ደርሶባቸዋል፤ በወጥመድ ተይዘውም ግራ ገብቶአቸዋል፤ እነርሱ ቃሌን ትተዋል፤ ታዲያ ምን ዐይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል?


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶች ፊት ፍርድን ተግባራዊ ያደርጉብሻል፤ በዚህ ዐይነት አመንዝራነትሽንና ለወዳጆችሽ የዝሙት ዋጋ መክፈልሽን እንድትተዪ አደርግሻለሁ።


ነገር ግን በቊጣ ከስሩ ተነቅሎ ወደ ምድር ተጣለ። ከበረሓ የሚነሣ የምሥራቅ ነፋስ አደረቀው፤ ፍሬዎቹም ረገፉ፤ ብርቱ የሆኑት ቅርንጫፎቹም ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።


እናንተ ሁለት እኅትማማቾች እንዳመነዘራችሁ ሁሉ ሴቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያመነዝሩ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከምድሪቱ ሁሉ ላይ የሴሰኝነት ስድነት እንዲወገድ አደርጋለሁ።


በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ።


ወደ ባሕር መግቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀምጣ ከተለያዩ የጠረፍ ከተሞች ለሚመጡ ነጋዴዎች አገናኝ ለሆነችው ለጢሮስ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራት፦ ‘ጢሮስ ሆይ! በፍጹም ውብ ነኝ ብለሻል።


መኖሪያሽ ባሕር ነው፤ ገንቢዎችሽ እንደ ተዋበች መርከብ ሠርተውሻል።


ከተፈጠርክበት ጊዜ አንሥቶ ክፋት ማድረግ እስከ ጀመርክበት ጊዜ ድረስ አካሄድህ ፍጹም ነበር፤


“የሰው ልጅ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ንጉሥ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ልብህ ስለ ታበየ እኔ አምላክ ነኝ በባሕሩ መካከል በአማልክት ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ ብለሃል። ምንም እንኳ አንተ በሐሳብህ አምላክ ነኝ ብትል ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


በንግድ ሥራም ባሳየኸው ታላቅ ብልኀት ብዙ ሀብት አግኝተሃል፤ ከሀብትህም ብዛት የተነሣ ኲራት ተሰምቶሃል።’


በአንተ ላይ አደጋ የሚጥሉ ጨካኞች ጠላቶችን አመጣብሃለሁ፤ እነርሱ በጥበብህና በብልኀትህ ያገኘኸውንና ያከማቸኸውን ያማረ ነገር ሁሉ ያጠፋሉ።


“እንግዲህ አድጎ እስከ ደመናት በደረሰ መጠን፥ ትዕቢት በሚሰማው በዚያ ዛፍ ላይ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የማደርገው ይህ ነው፤


ብዙ ሕዝቦች አንተን አይተው እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ ሰይፌን በፊታቸው በማነሣበት ጊዜ ንጉሦቻቸው በአንተ ምክንያት በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤ አንተ በምትወድቅበት ቀን እያንዳንዳቸው በየጊዜው ለሕይወታቸው በመፍራት ይርበደበዳሉ።”


ብዙ ተዋጊዎችን ስለሚማርክ ልቡ ይታበያል፤ ከዚያም በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ይፈጃል፤ ይሁን እንጂ በድል አድራጊነቱ ጸንቶ አይኖርም።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”


ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።


跟着我们:

广告


广告