Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የንግድ ሸቀጥ ሀብትሽ ሁሉ፥ መርከብ ነጂዎችሽ ሁሉ፥ በመርከብ ውስጥ የሚያገለግሉ ጠጋኞችሽና ነጋዴዎችሽ ሁሉ፥ በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩ ወታደሮች ሁሉ፥ መርከቦችሽ ሲሰባበሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ ባሕር ይሰጥማሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሀብትሽ፥ ሸቀጥሽ፥ ንግድሽ፥ መርከበኞችሽ፥ መርከብ መሪዎችሽ፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ፥ ሸቀጥሽን የሚነግዱ፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ወታደሮችሽ ሁሉ፥ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በውድቀትሽ ቀን ወደ ባሕር ልብ ይወድቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ኀይ​ል​ሽና ዋጋሽ፥ ንግ​ድ​ሽም፥ መር​ከ​በ​ኞ​ች​ሽም፥ መር​ከብ መሪ​ዎ​ች​ሽም፥ ሰባ​ራ​ሽን የሚ​ጠ​ግኑ ነጋ​ዴ​ዎ​ች​ሽም፥ በአ​ን​ቺም ዘንድ ያሉ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ሁሉ በው​ስ​ጥሽ ከአ​ሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወ​ደ​ቅ​ሽ​በት ቀን በባ​ሕር ውስጥ ይጠ​ፋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ብልጥግናሽና ሸቀጥሽ ንግድሽም መርከበኞችሽም መርከብ መሪዎችሽም ሰባራሽንም የሚጠግኑ ነጋዴዎችሽም በአንቺም ዘንድ ያሉ ሰልፈኞችሽ ሁሉ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በወደቅሽበት ቀን በባሕር ውስጥ ይወድቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:27
19 交叉引用  

ለመሞት በምትቃረብበት ቀን ሀብትህ አይጠቅምህም፤ ደግነት ግን የሕይወት ዋስትና ይሆንልሃል።


በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት በወሩም መባቻ ዕለት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥


ሀብትሽ ይማረካል፤ የንግድ ዕቃሽ ይዘረፋል፤ ቅጥርሽ ይፈርሳል፤ የተዋቡ ቤቶችሽ ይፈራርሳሉ፤ ድንጋዮችሽ፥ ሳንቃዎችሽና ፍርስራሹ ወደ ባሕር ይጣላሉ።


ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን የሚያሰጡበት አለት ብቻ አግጥጦ ይቀራል፤ ከተማይቱ ዳግመኛ አትታደስም፤ ይህም የሚሆነው እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ ተናገርኩ ነው።”


መጨረሻሽ አስፈሪ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍጻሜሽ ይሆናል፤ ሰዎች ቢፈልጉሽ እንኳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቶ አያገኙሽም፤” እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


“ከብልጽግናሽ ብዛት የተነሣ ከተርሴስ ጋር ንግድ በመለዋወጥ በአንቺ ዕቃዎች ለውጥ ከእርስዋ ብር፥ ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስ ታገኚ ነበር።


የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ለሸቀጥሽ ልዋጭ የከበሩ ድንጋዮች፥ ወርቅና ምርጥ የሆኑ ቅመማ ቅመሞች ያቀርቡልሽ ነበር።


የተዋቡ ልብሶችን፥ ሐምራዊ ጨርቆችንና፥ በእጅ ሥራ ያጌጡ ልብሶችን፥ ደማቅ የሆኑ ሥጋጃዎችን፥ በደንብ በተገመዱ ሲባጎዎችና ገመዶችን አጥብቀው በማሰር ይሸጡልሽ ነበር።


ቀዛፊዎችሽ አውጥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ወሰዱሽ፤ ኀይለኛውም የምሥራቅ ነፋስ አንገላትቶ በባሕሩ ውስጥ ሰባበረሽ።


መርከበኞቹ ወደ ባሕር ሲሰጥሙ ያሰሙት ጩኸት በባሕር ዳር ያሉትን አገሮች አንቀጠቀጡ።


አሁን ግን በጥልቁ ባሕር ውስጥ ተሰባብረሽ ቀርተሻል፤ የሸቀጥ ዕቃሽና ለአንቺ ያገለገሉ ሰዎች ሁሉ ከአንቺ ጋር አብረው ጠፍተዋል፤’


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥


አንተን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ይጥሉሃል፤ በባሕሩም መካከል አሠቃቂ የሆነ ሞት ትሞታለህ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤


ጢሮስ ለራስዋ መጠበቂያ ብዙ ምሽጎችን ሠርታለች፤ ብዛቱ እንደ ትቢያና እንደ ዐፈር የበዛ ብርና ወርቅ አከማችታለች።


跟着我们:

广告


广告