Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ቀዛፊዎችሽ አውጥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ወሰዱሽ፤ ኀይለኛውም የምሥራቅ ነፋስ አንገላትቶ በባሕሩ ውስጥ ሰባበረሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ቀዛፊዎችሽ፣ ወደ ጥልቁ ባሕር ይወስዱሻል፤ የምሥራቁ ነፋስ ግን፣ በባሕሩ መካከል ይሰባብርሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ውኆች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ልብ ሰበረሽ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ወደ ትልቁ ውኃ አመ​ጡሽ፤ የም​ሥ​ራቅ ነፋስ በባ​ሕር ውስጥ ሰበ​ረሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ትልቁ ወኃ አመጡሽ፥ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ውስጥ ሰበረሽ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:26
13 交叉引用  

በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ የተርሴስ መርከቦች ሆኑ።


እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤ አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን በዐይናችን አየን፤ እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።


እናንተ በባሕር ላይ የምትመላለሱ የተርሴስ መርከበኞች! የምትኰሩባት ወደብ ስለ ተደመሰሰች በዋይታ አልቅሱ!


ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።


ትቢያ በምሥራቅ ነፋስ እንደሚበተን፥ ሕዝቤን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። ፊቴን ከእነርሱ መልሼ ጀርባዬን እሰጣቸዋለሁ። ጥፋት በሚመጣባቸውም ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።”


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ማንም ሊኖርባቸው እንደማይችል እንደ ፈራረሱ ከተሞች ባድማ አደርግሻለሁ፤ ጥልቅ ከሆነ ውቅያኖስ በሚገኝ ውሃ እሸፍንሻለሁ፤


የንግድ ሸቀጥ ሀብትሽ ሁሉ፥ መርከብ ነጂዎችሽ ሁሉ፥ በመርከብ ውስጥ የሚያገለግሉ ጠጋኞችሽና ነጋዴዎችሽ ሁሉ፥ በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩ ወታደሮች ሁሉ፥ መርከቦችሽ ሲሰባበሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ ባሕር ይሰጥማሉ።


አሁን ግን በጥልቁ ባሕር ውስጥ ተሰባብረሽ ቀርተሻል፤ የሸቀጥ ዕቃሽና ለአንቺ ያገለገሉ ሰዎች ሁሉ ከአንቺ ጋር አብረው ጠፍተዋል፤’


አንተን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ይጥሉሃል፤ በባሕሩም መካከል አሠቃቂ የሆነ ሞት ትሞታለህ።


ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ “የሰሜናዊ ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ” የሚባል ኀይለኛ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ወደ ባሕሩ መጣባቸው።


ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቊልል ጋር በመጋጨቱ ቊልቊል ተደፋ፤ በስተፊቱም ወደ ታች ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊት የተነሣ ይሰባበር ጀመር።


መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራይቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ሕዝቦችና፥ ሰዎች፥ ወገኖችና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ናቸው፤


跟着我们:

广告


广告