ሕዝቅኤል 27:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የይሁዳና የእስራኤል ነጋዴዎች ለሸቀጥሽ ዋጋ የሚኒት አገር ስንዴ፥ ማሽላ፥ ማር፥ የወይራ ዘይትና ቅመማ ቅመም ይከፍሉሽ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ ‘ይሁዳና እስራኤል እንኳ ከአንቺ ጋራ ተገበያይተዋል፤ የሚኒትን ስንዴ፣ ጣፋጭ ቂጣ፣ ማር፣ ዘይትና በለሳን በማምጣት በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ዕቃዎችሽን በሚኒት ስንዴ፥ ጣፋጭ ዳቦ፥ ማር፥ ዘይትና በለሳን ይለውጡ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ይሁዳና እስራኤል ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ስንዴንም ይሸምቱልሽ ነበር፤ ሰሊሆትንና በለሶንን፥ ዘይትንና የተወደደ ማርን፥ ርጢንንም ከአንቺ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ሰጡሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጕቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር። 参见章节 |