ሕዝቅኤል 27:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የሶርያ ሕዝብ የንግድ ሸቀጥሽን ሁሉና ሌሎችንም ብዙ ዕቃዎች ይገዙሽ ነበር፤ በወሰዱአቸውም ዕቃዎች ምትክ በሉር፥ ሐምራዊና በጥልፍ ያጌጠ ልብስ፥ ቀጭን ሐር፥ ከዛጎል የተሠሩ ጌጣጌጦችና ቀይ ዕንቊ ይሰጡሽ ነበር፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ ‘ምርትሽ ብዙ እንደ መሆኑ፣ ሶርያ ከአንቺ ጋራ ትገበያይ ነበር፤ ሸቀጥሽንም በበሉር፣ በሐምራዊ ጨርቅ፣ በወርቀ ዘቦ፣ በጥሩ በፍታ፣ በዛጐልና በቀይ ዕንቍ ይለውጡ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የሶርያም ሰዎች ከገንዘብሽ ብዛት የተነሣ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ከአንቺም ጋር አንድ ከሆኑ ከብዙ ሰዎች ጋር ትነግጂ ነበር፤ ነጭ ሐርንና ዕንቍን፥ ቀይ ሐርንና ወርቀ ዘቦን ከርከዴን የሚባል ዕንቍንና ልባንጃም የሚባል ሽቱን ከተርሴስ ያመጡልሽ ነበር፤ ገበያሽንም ረዓሙትና ቆርኮር መሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከሥራሽ ብዛት የተነሣ ሶርያ ነጋዴሽ ነበረች በበሉርና በቀይ ሐር በወርቀ ዘቦም በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር። 参见章节 |