Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከሮድ አገር ሰዎች ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ በባሕር ዳር የሚገኙ አገሮች ሕዝቦች ሸቀጥሽን ወስደው በምትኩ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ያመጡልሽ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ ‘የድዳን ሰዎች ከአንቺ ጋራ ተገበያዩ፤ ብዙ የጠረፍ አገሮችም የንግድ ደንበኞችሽ ነበሩ፤ በዝኆን ጥርስና በዞጲ ሸቀጥሽን ይገዙ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የድዳን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የሮ​ድ​ያን ልጆ​ችም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደ​ስ​ያት ሰዎ​ችም የዝ​ኆን ጥርስ ይነ​ግ​ዱ​ልሽ ነበር፤ ከዚ​ያም የመጡ ሰዎች ዋጋ​ሽን ይሰ​ጡሽ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የድዳን ሰዎች ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:15
13 交叉引用  

የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባና ደዳን ናቸው።


ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የደዳንም ዘሮች አሹራውያን፥ ሌጡሻውያንና ሌኡማውያን ናቸው።


ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤


የኩሽ ልጆች ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው፤ የራዕማ ወንዶች ልጆች ሳባና ድዳን ናቸው።


ሰሎሞንም በኪራም አገልጋዮች አማካይነት ወደ ተርሴስ የሚጓዙ መርከቦች ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመቱ ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


ስለ ዐረብ አገር የተነገረውም ቃል ይህ ነው፤ ከጭነት ግመሎቻችሁ ጋር በዐረብ በረሓ የምትሰፍሩ እናንተ የደዳን ሕዝብ ሆይ፥


የዔሳውን ዘር በምቀጣበት ጊዜ መከራን ስለማመጣባቸው፥ የደዳን ከተማ ሕዝብ ሆይ! ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሩጡ! በዋሻም ተሸሸጉ!


ስለዚህ አሁን ኤዶምን እንደምቀጣና በዚያም ያሉትን ሰዎችና እንስሶች በሙሉ እንደማጠፋ አሳውቃለሁ፤ ከቴማን ከተማ እስከ ደዳን ከተማ ድረስ ባድማ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ሕዝቡም በጦርነት ያልቃሉ፤


የደዳን ሕዝብ ስለ ሸቀጥሽ ልዋጭ የኮርቻ ልብስ ያመጣልሽ ነበር።


ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ”


በመርከባቸው የተጫነውም ወርቅ፥ ብር፥ የከበረ ድንጋይ፥ ዕንቊ፥ ቀጭን ልብስ፥ ሐምራዊ ልብስ፥ ሐር ልብስ፥ ቀይ ልብስና መልካም መዓዛ ያለው እንጨት ሁሉ፥ ከዝኆን ጥርስ፥ ውድ ከሆነ እንጨት፥ ከነሐስ፥ ከብረትና ከእብነበረድ የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥


跟着我们:

广告


广告