Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ከብልጽግናሽ ብዛት የተነሣ ከተርሴስ ጋር ንግድ በመለዋወጥ በአንቺ ዕቃዎች ለውጥ ከእርስዋ ብር፥ ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስ ታገኚ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ ተርሴስ ነጋዴሽ ነበረች፥ በብርና በብረት በቆርቆሮና በእርሳስ ዕቃሽን ለወጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ከኀ​ይ​ልሽ ሁሉ ብዛት የተ​ነሣ የተ​ር​ሴስ ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ገበ​ያ​ሽን ብር፥ ወር​ቅና ብረት፥ ቆር​ቆ​ሮና እር​ሳ​ስም አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከብልጥግናሽ ሁሉ ብዛት የተነሣ ተርሴስ ነጋዴሽ ነበረች፥ በብርና በብረት በቈርቈሮና በእርሳስ ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:12
22 交叉引用  

የያዋን ልጆች፦ የኤሊሻ፥ የተርሴስ፥ የኪቲምና የሮዳኒም ሰዎች ናቸው።


ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።


ሰሎሞንም በኪራም አገልጋዮች አማካይነት ወደ ተርሴስ የሚጓዙ መርከቦች ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመቱ ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።


እጅግ የተዋቡ ዕቃዎችንና የተርሴስ መርከቦችን እንኳ ያሰጥማል፤


የተርሴስ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ ወደብ ስለሌላችሁ ልክ በአባይ ወንዝ ዳር እንደሚደረገው ምድራችሁን እረሱ።


እናንተ በባሕር ላይ የምትመላለሱ የተርሴስ መርከበኞች! የምትኰሩባት ወደብ ስለ ተደመሰሰች በዋይታ አልቅሱ!


እናንተ በባሕር ጠረፍ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! በዋይታ እያለቀሳችሁ ወደ ተርሴስ ተሻገሩ።


የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።


ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል።


ከአርዋድ የመጡ ወታደሮች የቅጽር ግንቦችሽን ይጠብቁ ነበር፤ ከጋማድም የመጡ ሰዎች ምሽጎችሽን ይጠብቁ ነበር፤ ጋሻዎቻቸውን በግንቦችሽ ላይ ሰቀሉ፤ የተዋብሽ እንድትሆኚ ያደረጉሽ እነርሱ ናቸው።


ከግሪኮች ከቱባልና ከሜሼክ ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ ባሪያዎችንና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ወስደሽ፥ በምትኩ ሸቀጥሽን ትሰጪአቸው ነበር፤


የሶርያ ሕዝብ የንግድ ሸቀጥሽን ሁሉና ሌሎችንም ብዙ ዕቃዎች ይገዙሽ ነበር፤ በወሰዱአቸውም ዕቃዎች ምትክ በሉር፥ ሐምራዊና በጥልፍ ያጌጠ ልብስ፥ ቀጭን ሐር፥ ከዛጎል የተሠሩ ጌጣጌጦችና ቀይ ዕንቊ ይሰጡሽ ነበር፤


የደማስቆ ሕዝብ ስለ ሸቀጥሽና ስለ ሌሎችም ዕቃዎችሽ ከሔልቦን የተገኘ የወይን ጠጅና ከሳሖር የተገኘ የበግ ጠጒር ይሰጡሽ ነበር።


የሸቀጥ ዕቃሽ በየሀገሩ ሲሠራጭ፥ የየሀገሩን ሕዝብ ፍላጎት ያሟላ ነበር፤ ከአንቺ በተትረፈረፈ ሀብትና ሸቀጥ የምድር ነገሥታትን አበልጽገሻል።


በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።


በንግድ ሥራም ባሳየኸው ታላቅ ብልኀት ብዙ ሀብት አግኝተሃል፤ ከሀብትህም ብዛት የተነሣ ኲራት ተሰምቶሃል።’


ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ”


ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።


በመርከባቸው የተጫነውም ወርቅ፥ ብር፥ የከበረ ድንጋይ፥ ዕንቊ፥ ቀጭን ልብስ፥ ሐምራዊ ልብስ፥ ሐር ልብስ፥ ቀይ ልብስና መልካም መዓዛ ያለው እንጨት ሁሉ፥ ከዝኆን ጥርስ፥ ውድ ከሆነ እንጨት፥ ከነሐስ፥ ከብረትና ከእብነበረድ የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥


跟着我们:

广告


广告