Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱ መኻል አገር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማቸዋል፤ በዙሪያሽ ካብ ይክባል፤ እስከ ቅጥሮችሽ ጫፍ ድረስ ዐፈር ይደለድልብሻል፤ ጋሻውንም በአንቺ ላይ ያነሣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ በአንቺ ላይ ምሽግ ይሠራል፥ ደለልም በአንቺ ላይ ይደለድላል፥ በአንቺም ላይ ጋሻ ያነሣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ አምባም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:8
9 交叉引用  

የኢዮአብ ወታደሮች ሼባዕ እዚያ መሆኑን ስለ ሰሙ ሄደው ከተማይቱን ከበቡ፤ በስተውጪ በኩል ቅጽሩን አስደግፈው የዐፈር ቊልል ሠሩ፤ ቀጥሎም ቅጽሩ እንዲወድቅ ከስሩ መቈፈር ጀመሩ።


“እነሆ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ለመያዝ ዐፈር ቈልለው ዙሪያዋን በመክበብ ላይ ናቸው፤ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር ከተማይቱ በእነርሱ እጅ እንድትወድቅ ያደርጓታል፤ እነሆ አንተ የተናገርከው ሁሉ መድረሱን ታያለህ፤


ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በመምጣት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል አስከበባት፤ ሠራዊቱም በከተማይቱም ዙሪያ ሰፈረ፤ በቅጥሩም ዙሪያ ዐፈር ቈለለ።


ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዛፎችን ቊረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደምሽግ ሆኖ የሚያገለግል ዐፈር ቈልሉ፤ እርስዋ በግፍ የተሞላች ስለ ሆነ መቀጣት የሚገባት ከተማ ናት፤


እነሆ ቀኝ እጁ ‘ኢየሩሳሌም!’ የሚል ጽሑፍ ያለበትን ፍላጻ አንሥቶ ይይዛል፤ እርሱም ሄዶ ምሽግ ማፍረሻዎችን እንዲያዘጋጅ፥ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ድንፋታ እንዲያሰማ፥ ምሽግ ማፍረሻዎችን ወደ ቅጽር በሮቹ እንዲያስጠጋ፥ ዐፈር ቈልሎ እንዲደለድልና የከበባ ምሽግ እንዲሠራ ይነግረዋል።


በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ”


በምሽግ ማፍረሻ መሣሪያ ቅጽሮችሽን ይመታል፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን በምሳር ያፈራርሳል፤


በነገሥታት ላይ ይሳለቃሉ፤ መሪዎቻቸውንም ይንቃሉ፤ በምሽጎቹ ሁሉ ላይ በመሳቅ ዐፈር ቈልለው ይይዙዋቸዋል።


ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል።


跟着我们:

广告


广告