ሕዝቅኤል 26:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጢሮስ ላይ አደጋ እንዲጥል የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከሰሜን በኩል አመጣባታለሁ፤ እርሱም ከታላቅ ሠራዊት ጋር በብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች በፈረሰኞችም ታጅቦ ይመጣል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋራ፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋራ ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶች፥ ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞች፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞችም፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብም ጋር በአንቺ ላይ አመጣለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነዖርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ። 参见章节 |