Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም፣ ‘ዕሠይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች፤ ደጆቿም ወለል ብለው ተከፈቱልኝ፤ እንግዲህ እርሷ ስለ ፈራረሰች እኔ እከብራለሁ’ ብላለችና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ “እሰይ የሕዝቦች በር የነበረች ተሰበረች፤ ወደ እኔም ተመለሰች፤ እርሷ ስለፈረሰች እኔ እሞላለሁ፤” ብላለችና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰ​በ​ረች፥ ጠፋ​ችም፥ ሕዝ​ቧም ወደ እር​ስዋ ተመ​ለሱ፤ ሞልታ የነ​በ​ረች አለ​ቀች ብላ​ለ​ችና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ፦ እሰይ፥ የአሕዛብ በር የነበረች ተሰብራለች ወደ እኔም ተመልሳለች፥ እርስዋ ፈርሳለችና እኔ እሞላለሁ ብላለችና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:2
27 交叉引用  

የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ይሠሩለት ዘንድ አናጢዎች፥ ግንበኞችና የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስይዞ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ።


“ይኸዋ! ይኸዋ! እኛ ራሳችን የሠራኸውን አየን!” እያሉ በመጮኽ ያሳጡኛል።


በእኔ ውድቀት “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ በኀፍረት ይሸማቀቁ።


አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፥ ሐሴትም ያድርጉ፤ ያንተን ማዳን የሚወዱ ዘወትር፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።


እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።


የጌባል፥ የዐሞን፥ የዐማሌቅ፥ የፍልስጥኤምና የጢሮስ ሰዎች ናቸው።


በቅጥር በሩ በኩል ዕለፉ፤ ለሰዎች መንገዱን አዘጋጁ፤ አውራ ጐዳናውን ሥሩ፤ ድንጋዮችን አስወግዱ፤ አርማውንም ለሕዝቦች ከፍ አድርጉ።”


በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ።


ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።


እግዚአብሔር ስለ ዐሞን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትምን? ወራሾች የሉትምን? ታዲያ ሚልኮም የተባለውን ጣዖት የሚያመልኩ ወገኖች የጋድን ነገድ አስለቅቀው በከተሞቹ የሰፈሩት ለምንድን ነው?


በአንድ ወቅት በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ እንዴት ብቸኛ ሆነች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው እንዴት ባል እንደ ሞተባት ሴት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፥ አሁን እርስዋ እንደ ባሪያ ሆነች።


ከእንግዲህ ወዲህ ዐሞን በመንግሥትነት እንዳትታወቅ ከምሥራቅ የሚመጡ ነገዶች ሞአብንና ዐሞንን እንዲወሩአቸው አደርጋለሁ።


“ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ በእጃችሁ በማጨብጨብና በእግራችሁም በመርገጥ የእስራኤልንም ምድር በንቀት ተመልክታችኋት ነበር።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሞአብና ኤዶም ‘ይሁዳ ከሌሎች ሕዝቦች አገሮች የተለየች አይደለችም’ በማለታቸው


በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት በወሩም መባቻ ዕለት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥


“ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ጠላቶች ‘እነሆ፥ እነዚያ የጥንት ተራራዎች የእኛ ሆነዋል!’ በማለት መጓደድ ጀምረዋል።


“እናንተ የጢሮስ፥ የሲዶናና የፍልስጥኤም አውራጃዎች ሕዝብ ሆይ፥ ምን እያደረጋችሁ ነው? እኔን ለመበቀል ይቃጣችኋልን? ይህ ከሆነ ሥራችሁ ወዲያው በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እንዲመለስ አደርጋለሁ።


ድንበሩ እስከ ተመሸገችው እስከ ጢሮስ ከተማ ይደርስና ወደ ራማ ይታጠፋል፤ ከዚያም መመለሻው የሜድትራኒያን ባሕር ሆኖ ወደ ሖሳ ይታጠፋል፤ እርሱም ማሐላብ፥ አክዚብ፥


跟着我们:

广告


广告