Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነሆ አሁን በወደቀችበት ቀን ደሴቶች ተንቀጠቀጡ፤ በላያቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ከዚህ ታላቅ ጥፋት የተነሣ ደነገጡ።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አሁን በመውደቂያሽ ቀን፣ በጠረፍ ያሉ አገሮች ተናወጡ፤ ከመፍረስሽም የተነሣ፤ በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶች ተደናገጡ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሁን በውድቀትሽ ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕር ያሉ ደሴቶችም ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አሁን በው​ድ​ቅ​ትሽ ቀን ደሴ​ቶች ይፈ​ራሉ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያሉ ደሴ​ቶች ከመ​ው​ጣ​ትሽ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አሁን በውድቀትሽ ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕርም ውስጥ ያሉ ደሴቶች ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:18
9 交叉引用  

“በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች እኔ ያደረግኹትን ሁሉ አይተዋል፤ ስለዚህም እጅግ ደንግጠው ተንቀጥቅጠዋል፤ በአንድነትም ተሰብስበው ወደ እኔ መጥተዋል።


የኤዶም አወዳደቅ ዜና ሲሰማ ምድር ትናወጣለች፤ የድንጋጤውም ጩኸት ከዚያ አልፎ እስከ ቀይ ባሕር ይሰማል።


የባቢሎን መያዝ ዜና ሲሰማ ምድር ትናወጣለች፤ ጩኸትዋም በሕዝቦች መካከል ይሰማል።”


ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ከተማ እንዲህ ይላታል፦ “ቊስለኞች ሲቃትቱና በመካከልሽ ግድያ ሲካሄድ ባወዳደቅሽ ድምፅ የጠረፉ አካባቢ አይናወጥምን?


“በባሕር ጠረፍ የሚኖሩ ሁሉ አንቺን ከገጠመሽ መጥፎ ዕድል የተነሣ ደንግጠዋል፤ ንጉሦቻቸውም እንኳ ሳይቀሩ ተሸብረዋል፤ በያንዳንዳቸውም ፊት ላይ ፍርሀት ይነበባል።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ።


跟着我们:

广告


广告