Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት በወሩም መባቻ ዕለት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ በዓሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ከወሩ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፥ በአሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 26:1
14 交叉引用  

ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ።


ይህም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ኢኮንያን ከተማረከ አምስት ዓመት ከአምስት ቀን ሆኖት ነበር፤


በተሰደድን በሰባተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሕዝብ መሪዎች ጥቂቶቹ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሊጠይቁኝ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።


በቊጣ ከተመላ ቅጣቴ ጋር ታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በእነርሱም ላይ በምወስደው እርምጃ እኔ እግዚአብሔር መሆን ያውቃሉ።’ ”


“የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ።


የንግድ ሸቀጥ ሀብትሽ ሁሉ፥ መርከብ ነጂዎችሽ ሁሉ፥ በመርከብ ውስጥ የሚያገለግሉ ጠጋኞችሽና ነጋዴዎችሽ ሁሉ፥ በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩ ወታደሮች ሁሉ፥ መርከቦችሽ ሲሰባበሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ ባሕር ይሰጥማሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥


በተሰደድን በዐሥረኛው ዓመት፥ በዐሥረኛው ወር፥ ከወሩም በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤


በተሰደድን በሃያ ሰባተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ በወሩም በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በተሰደድን በስድስተኛው ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ቀን፥ ከይሁዳ የተሰደዱት ሕዝብ መሪዎች በቤቴ ከእኔ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ፥ የልዑል እግዚአብሔር ኀይል ድንገት በእኔ ላይ ወረደ።


እስራኤልን በመልካም መሬት ላይ እንደ ተተከለች የዘንባባ ዛፍ ሆና አየኋት፤ እስራኤላውያን ግን ልጆቻቸውን ለዕርድ አቀረቡ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤


ይህም የፍርድ ቃል የሐድራክ አዋሳኝ በሆነችው ሐማትና፥ ብዙ ጥበብ ባላቸው በጢሮስና በሲዶና ከተሞችም ይደርስባቸዋል።


跟着我们:

广告


广告