Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 25:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የራባን ከተማ የግመሎች ማሰማርያ፥ መላውንም የዐሞን አገር የበጎች መዋያ አደርገዋለሁ፤ በዚህም ዐይነት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የረባት ከተማ የግመሎች መሰማሪያ፣ አሞንንም የበጎች መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ራባን የግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የአ​ሞ​ንን ከተማ ለግ​መ​ሎች ማሰ​ማ​ሪያ፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ለመ​ንጋ መመ​ሰ​ጊያ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 25:5
18 交叉引用  

በዚያን ጊዜ ኢዮአብ ራባ ተብላ የምትጠራውን የዐሞናውያንን ከተማ ለመያዝ የሚያደርገውን ዘመቻ በመቀጠል የከተማ ውሃ የሚገኝበትን ምሽግ ያዘ።


በምድር ሁሉ ላይ ጌታና ሁሉን ቻይ አምላክ አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንክ ይወቁ።


የሶርያ ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው ባድማዎች ይሆናሉ፤ በጎችና ከብቶች በዚያ ይሰማራሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።


ቤተ መንግሥቱ ሳይቀር ወና ይሆናል፤ መናገሻ ከተማውም የተፈታ ምድረ በዳ ይሆናል፤ ቤቶችና የመጠበቂያ ማማዎች ይፈርሳሉ፤ የሜዳ አህዮች መራገጫና የመንጋ መሰማርያ ይሆናሉ።


እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦራውያን እጅ በመታደግ አድነን።”


ስለዚህ የአሞን ከተማ በሆነችው በራባ ላይ የጦርነት ክተት ጥሪ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል፤ እርስዋ፥ በፍርስራሽ ክምር የተሞላች ባድማ ትሆናለች፤ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን አስቀድመው እነርሱን የበዘበዙአቸውን መልሰው ይበዘብዛሉ።


ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ።


“አንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላብህ የእስራኤል መሪ! ለመጨረሻ ጊዜ የምትቀጣበት ቀን እነሆ ቀርቦአል።


“ ‘ሰይፉን ወደ አፎቱ መልሱ! በተፈጠራችሁበት ስፍራ፥ በተወለዳችሁበትም አገር እፈርድባችኋለሁ፤


በዚህም ዐይነት ሕዝቅኤል ለእናንተ ምልክት ይሆናል፤ እርሱ እንዳደረገውም ታደርጋላችሁ፤’ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሞአብና ኤዶም ‘ይሁዳ ከሌሎች ሕዝቦች አገሮች የተለየች አይደለችም’ በማለታቸው


በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ”


ግብጽን የሚያጋይ እሳት በማቀጣጥልበት ጊዜ፥ እንዲሁም የደጋፊዎችዋ ኀይል በተንኰታኰተ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።


እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።


በዚህም ዐይነት ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


በባሕር ዳር ያለው ምድራችሁ የከብት ማሰማሪያ፥ የእረኞች መኖሪያና የመንጋዎች ማደሪያ በረት ይሆናል።


ከረፋያውያን ወገን ንጉሥ ዖግ የመጨረሻው ነበር፤ አልጋው ከብረት የተሠራ ሆኖ በይፋ በታወቀው መለኪያ ቁመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ያኽል ነበር። እርሱም ራባ ተብላ በምትጠራው በዐሞናውያን ከተማ እስከ አሁን ይታያል።


跟着我们:

广告


广告