Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 25:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እኔ ሞአብን እቀጣለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሞዓብንም እቀጣለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በሞዓብም ላይ ፍርድ እሰጣለሁ። እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሞ​አ​ብም ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በሞዓብም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 25:11
20 交叉引用  

እንደዚህ ቢያደርጉ መንግሥታትን ለማሸነፍ፥ አሕዛብንም ለመቅጣት፥


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


እናንተን ከከተማይቱ አስወጥቼ ለባዕዳን ሕዝቦች አሳልፌ በመስጠት እፈርድባችኋለሁ።


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶች ፊት ፍርድን ተግባራዊ ያደርጉብሻል፤ በዚህ ዐይነት አመንዝራነትሽንና ለወዳጆችሽ የዝሙት ዋጋ መክፈልሽን እንድትተዪ አደርግሻለሁ።


ከእንግዲህ ወዲህ ዐሞን በመንግሥትነት እንዳትታወቅ ከምሥራቅ የሚመጡ ነገዶች ሞአብንና ዐሞንን እንዲወሩአቸው አደርጋለሁ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የኤዶም ሕዝብ በይሁዳ ላይ ጭካኔ የተሞላበት በቀል ፈጽመዋል፤ ይህንንም በማድረጋቸው በደለኞች ሆነዋል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በቊጣ ከተመላ ቅጣቴ ጋር ታላቅ በቀል እበቀላቸዋለሁ፤ በእነርሱም ላይ በምወስደው እርምጃ እኔ እግዚአብሔር መሆን ያውቃሉ።’ ”


የራባን ከተማ የግመሎች ማሰማርያ፥ መላውንም የዐሞን አገር የበጎች መዋያ አደርገዋለሁ፤ በዚህም ዐይነት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


እዚያ ያለ ስጋት ይኖራሉ፤ ቤቶችን ይሠራሉ፤ ወይንም ይተክላሉ፤ በንቀት ይመለከቱአቸው የነበሩትን ጐረቤቶቻቸውን ሁሉ እቀጣለሁ፤ እስራኤላውያን ግን ያለ ስጋት በመተማመን ይኖራሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


በደቡባዊ ግብጽ ጳጥሮስ የተባለውን ከተማ ባድማ አደርጋለሁ፤ በሰሜን በኩል በምትገኘው በጾዓን ከተማ ላይም እሳት አቀጣጥላለሁ፤ የቴብስንም ከተማ በፍርድ እቀጣለሁ።


ግብጽን በዚህ ዐይነት በምቀጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


የእስራኤል ምድር ባድማ በመሆኑ እንደ ተደሰታችሁ እኔም የሴኢርን ተራራና የኤዶምን ግዛት ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።”


ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ክብሬን በሕዝቦች መካከል እገልጣለሁ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ተግባራዊ ያደረግኹትን ፍርዴንና እነርሱን የቀጣሁበትን ኀይሌን ያያሉ።


በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።


“በኀይለኛ ቊጣዬ በእናንተ ላይ ፍርዴን ተግባራዊ አድርጌ በምቀጣችሁ ጊዜ በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች የመሳለቂያ፥ የሽሙጥ፥ የማስጠንቀቂያ የድንጋጤ ምክንያት ትሆናላችሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


በዚህም ምክንያት እኔ ልዑል እግዚአብሔር በአንቺ በኢየሩሳሌም ላይ በቊጣ የተነሣሁብሽ መሆኔን እገልጥልሻለሁ፤ ሕዝቦች ሁሉ እያዩ በፍርድ እቀጣሻለሁ።


እነዚያን እግዚአብሔርን የማያመልኩትን ሰዎች ባደረጉአቸው ክፉ ነገሮች ምክንያት ይቀጣቸዋል፤ እግዚአብሔርም በእውነቱ በእነዚህ እርሱን በማያመልኩ ኃጢአተኞች ላይ በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ይፈርድባቸዋል።”


跟着我们:

广告


广告