Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 24:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በሐዘንም መንሰቅሰቅህን ሰው አይስማህ፤ ለሟችዋ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህንም በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ አፍህን አትሸፍን፤ የእዝን እንጀራ አትብላ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ድምፅህን ዝቅ አድርገህ በሐዘን አንጐራጕር እንጂ ለሞተው አታልቅስ። ጥምጥምህን ከራስህ አታውርድ፤ ጫማህንም አታውልቅ፤ አፍህ ድረስ አትሸፋፈን፤ የዕዝን እንጀራም አትብላ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዝምታ ተክዝ፥ ለሙታን አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈርህን አትሸፍን፥ የዕዝን እንጀራም አትብላ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በቀስታ ተክዝ፥ ለምዋቾችም አታልቅስ፥ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፥ ከንፈሮችህንም አትሸፍን የሰዎችንም እንጀራ አትብላ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 24:17
18 交叉引用  

ዳዊትም ሐዘኑን በመግለጥ ጫማ ሳያደርግ ራሱን ተከናንቦ የደብረ ዘይትን አቀበት እያለቀሰ ወጣ፤ የተከተሉትም ሁሉ ደግሞ ራሳቸውን ተከናንበው ያለቅሱ ነበር።


በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ።


ይህ ሁሉ እንዲደርስብኝ ያደረግኸው አንተ ስለ ሆንክ ዝም እላለሁ፤ አንድ ቃል እንኳ አልናገርም።


ጸጥ ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ፤ በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን “ጫማህንና የማቅ ልብስህን አውልቀህ በባዶ እግርህ ሂድ” ብሎ አዘዘው። ኢሳይያስም ለቃሉ በመታዘዝ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ይመላለስ ነበር።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የተከበረ ዘውዳቸው ከራሳቸው ስለ ወደቀ ንጉሡና ንግሥት እናቱ ከዙፋናቸው እንዲወርዱ ንገራቸው።


ጠዋት በማለዳም ከሰዎች ጋር እነጋገር ነበር፤ በዚያች ምሽት ሚስቴ ሞተች፤ በሚቀጥለውም ቀን ልክ እንደ ተነገረኝ አደረግሁ።


በራሳቸው ላይ ከበፍታ የተሠራ መጠምጠሚያ ይጠምጥሙ፤ በወገባቸውም ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ልብስ ይልበሱ፤ ማናቸውም ላብ የሚያመጣ መታጠቂያ አይታጠቁ።


በዚያም ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ መባ ማቅረብ አይችሉም፤ መሥዋዕታቸውም እግዚአብሔርን አያስደስትም፤ የእነርሱ እንጀራ ሲርባቸው የሚበሉት እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ አይደለም፤ ስለዚህ ለእነርሱ የእዝን እንጀራ ይሆናል፤ እርሱንም የሚመገብ ሁሉ ይረክሳል።


ከዚህ በኋላ ሙሴ አሮንን፥ እንዲሁም አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ሁለቱን የአሮንን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ “ለሐዘን ብላችሁ ጠጒራችሁን አትላጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቊጣውን ያወርዳል፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር በተላከ እሳት ስለሞቱት ልጆች እንዲያለቅሱ ተፈቅዶላቸዋል።


“በዚህ ዐይነት የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበት ሰው የተቀዳደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጒሩን አያበጥር፥ ከንፈሩን ይሸፍን፤ ከዚያም በኋላ ‘እኔ የረከስኩ ነኝ! የረከስኩ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ።


“ሊቀ ካህናቱ የቅባት ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበትና የክህነትንም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ስለ ሆነ፥ ሰው በሞተ ጊዜ ሐዘኑን ለመግለጥ ጠጒሩን አይላጭ፤ ልብሱንም አይቅደድ፤


በቤተ መንግሥት የሚያሰሙት ዘፈን በዚያን ቀን ወደ ለቅሶ ይለወጣል፤ የብዙ ሰው ሬሳ በየቦታው ወድቆ ይገኛል፤ በዝምታም በየስፍራው ይጣላል።”


‘ራእይ እናያለን፥ ትንቢት እንናገራለን’ የሚሉ ሁሉ ስለማይሳካላቸው ይዋረዳሉ፤ እግዚአብሔርም መልስ ስለማይሰጣቸው ከማፈራቸው የተነሣ ፊታቸውን በእጃቸው ሸፍነው ይሄዳሉ።”


እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ስለዚህ የዓለም ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ጸጥ ይበል።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ምኲራብ አለቃው ቤት በደረሰ ጊዜ የሐዘን እምቢልታ ነፊዎችንና እየተራወጡ በመጮኽ የሚያለቅሱትን ሰዎች አየ።


跟着我们:

广告


广告