Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 24:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ ልዑል እግዚአብሔር ‘አንድ ነገር የማደርግበት ጊዜ ቀርቦአል፤ አልገታም፤ አልምርም፤ ሐሳቤን አለውጥም፤ እንደ አካሄድሽና እንደ ሥራሽ እፈርድብሻለሁ’ ” ብዬ ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ ‘እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ የምሠራበትም ጊዜ ደርሷል፤ ወደ ኋላ አልልም፤ አልራራም፤ አላመነታምም። እንደ መንገድሽና እንደ ተግባርሽ ይፈረድብሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እመ​ጣ​ለሁ፤ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ውም፤ አል​ራ​ራም፤ አል​ጸ​ጸ​ትም፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽና እንደ ሥራ​ሽም እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ የሰ​ውን ደም እንደ አፈ​ሰ​ስሽ እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ት​ሽም ተበ​ቅዬ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ስም​ሽም ጐሰ​ቈለ፥ ብዙ ኀዘ​ን​ንም ታዝ​ኛ​ለሽ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ ይመጣል፥ እኔም አደርገዋለሁ፥ አልመለስም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም፥ እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 24:14
30 交叉引用  

ሸሽቶ ለማምለጥ ቢሞክርም ነፋሱ ያለ ርኅራኄ በእርሱ ላይ ያይልበታል፤


እርሱ በተናገረ ጊዜ ዓለም ተፈጠረ፤ በትእዛዙም ሁሉ ነገር ጸንቶ ቆመ።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው። እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልእኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም።


ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”


እግዚአብሔር ያቀደውን ተግባራዊ አድርጎ እስኪፈጽም ድረስ ቊጣው ከቶ አይገታም፤ ወደ ፊት ሕዝቡ ይህን ሁሉ በግልጥ ይረዱታል።


ይሁዳ ሆይ! ይህ ሁሉ የደረሰብሽ በአካሄድሽና በክፉ ሥራሽ ምክንያት ነው፤ ይህም ሁሉ የመረረ መከራ የመጣብሽ በኃጢአትሽ ምክንያት ስለ ሆነ ወደ ሰውነትሽ ዘልቆ ልብሽን አቊስሎታል።


በልጅነትሽ ወራት ያደረግኹልሽን ሁሉ ረሳሽ፤ በፈጸምሽውም ክፉ ሥራ አስቈጣሽኝ፤ ስለዚህ እኔም በሠራሽው ኃጢአት መጠን ዋጋሽን እንድትቀበይ አደረግሁ፤ በፈጸምሽው አጸያፊ ሥራ ሁሉ ላይ የዝሙትን ርኲሰት መጨመርሽ ለምን ይሆን?” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”


“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።


ስለዚህ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በኀይለኛ ቊጣዬም አጠፋቸዋለሁ፤ በደላቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል።


አንቺን ከመጥላታቸው የተነሣ የደከምሽበትን ሁሉ ይወስዱብሻል፤ እርቃንሽንም አስቀርተው እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተ ሥጋሽ እንዲጋለጥ ያደርጋሉ፤ የተቃጠለ ፍትወትሽና ዘማዊነትሽ፥ ይህ ሁሉ እንዲደርስብሽ አድርጎአል፤ ለሕዝቦች ሁሉ የፍትወት መጠቀሚያ ዘማዊት ሆነሽ በጣዖቶቻቸው ራስሽን አረከስሽ።


እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦


በዚያን ቀን ‘አንዳች ነገር ይደርስብናል’ ብለው ያልተጠራጠሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራራት መልእክተኞች በእኔ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ እነርሱም በግብጽ ላይ በእርግጥ በሚመጣው ጥፋት ምክንያት ይጨነቃሉ።”


አኗኗራቸውና ሥራቸው ሁሉ መጥፎ ስለ ነበረ ፈረድኩባቸው፤ በባዕዳን አገሮችም እንዲበተኑ አደረግሁ።


“ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አሁን መጥፊያችሁ ደርሶአል። ቊጣዬን አወርድባችኋለሁ፤ እንደ አካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ ስለ ርኲሰታችሁም ሁሉ እቀጣችኋለሁ።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም። በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


“አሁን እኔ በቅርቡ ቊጣዬንና መዓቴን አወርድባችኋለሁ፤ እንዳካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ፤ በአጸያፊ ድርጊታችሁም ምክንያት እቀጣችኋለሁ።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ስለዚህ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ራርቼም አልተዋቸውም፤ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እኔ ቢጮኹም አላደምጣቸውም።”


ስለዚህ አልራራላቸውም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነርሱ በሌሎች ላይ ያደረጉትን ሁሉ በእነርሱ ላይ መልሼ አደርግባቸዋለሁ።”


“እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ባለመራራት ቅጣት ላመጣባችሁ ወሰንኩ።


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእኔ የእግዚአብሔር ኀይል ውሱን ነውን? ቃሌ በእናንተ ዘንድ የሚፈጸም ወይም የማይፈጸም መሆኑን አሁን ታያለህ!”


እግዚአብሔር እንደ ሰው አይዋሽም፤ ሐሳቡንም እንደ ሰው አይለውጥም የሰጠውን ተስፋ ሁሉ ይፈጽማል፤ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።


የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ሆኖ ከመላእክቱ ጋር ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”


የእስራኤል ክብር የሆነ እግዚአብሔር አያብልም፤ ሐሳቡንም አይለውጥም፤ እርሱ እንደ ሰው ስላልሆነ ሐሳቡን አይለውጥም።”


跟着我们:

广告


广告