Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ማመንዘር ስለ ለመዱና እጆቻቸውም በደም ስለ ተበከሉ፥ በእነዚያ በአመንዝሮቹና በነፍሰ ገዳዮቹ ላይ ጻድቃን ይፈርዱባቸዋል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ጻድቃን ግን ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባቸውን ፍርድ ይፈርዱባቸዋል። አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል፤ ምክንያቱም አመንዝሮች ናቸውና፥ ደምም በእጃቸው አለና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ሴቶቹ አመ​ን​ዝ​ሮች ናቸ​ውና፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ደም አለና ጻድ​ቃን ሰዎች በአ​መ​ን​ዝ​ሮ​ቹና በደም አፍ​ሳ​ሾቹ ሴቶች ላይ በሚ​ፈ​ረ​ደው ፍርድ ይፈ​ር​ዱ​ባ​ቸ​ዋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:45
17 交叉引用  

ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።


ልብሶችሽ በንጹሖችና በድኾች ደም ተበክለዋል። “ነገር ግን ይህን ሁሉ አድርገሽ፥ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አይቈጣም!’ ትያለሽ፤ ነገር ግን ‘እኔ ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሽ በመካድሽ ምክንያት እኔ እግዚአብሔር እፈርድብሻለሁ።


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ እንዲህ በመናገራቸው፥ ቃሌ በአፍህ እንደ እሳት ይሆናል፤ ሕዝቡም እንደ እንጨት ሆነው እሳቱ ይበላቸዋል።”


እነርሱ በደም የረከሱ ስለ ሆኑ ሰው ልብሳቸውን እንኳ ለመንካት አይደፍርም፤ እነርሱ ግን እንደ ዕውሮች በመንገድ ላይ ይንከራተታሉ።


ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል።


እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል።


ወንዶች ወደ አመንዝራ ሴቶች እንደሚሄዱ ሁሉ፥ እነዚያም ከበረሓ የመጡ ወንዶች ኦሆላና ኦሆሊባ ከተባሉት ከእነዚያ ከረከሱ ሴቶች ጋር አመነዘሩ።


በከተማይቱ ውስጥ ግድያ ተፈጽሞአል፤ ደሙም የፈሰሰው ትቢያ በሚሸፍነው መሬት ላይ አይደለም፤ ነገር ግን ደሙ የፈሰሰው ምንም በማይሸፍነው ገላጣ አለት ላይ ነው።


ልጆቼ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ እናታችሁ ሚስቴ ስላልሆነችና እኔም ባልዋ ስላልሆንኩ የዝሙት አመለካከትዋንና አመንዝራነትዋን እንድታስወግድ ውቀስዋት።


በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።


አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ቢያመነዝር፤ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤


የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ አመንዝራ ብትሆን አባትዋን ታስነውራለች፤ እርስዋ በእሳት ተቃጥላ ትሙት።


ነገር ግን አገልጋዮቼ በሆኑት በነቢያት አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁ ያስተላለፍኩትን ሕግና ትእዛዝ ባለመጠበቃቸው ተቀጥተው የለምን? ስለዚህ በበደላቸው ተጸጸተው ‘የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት እንደ ሥራችንና እንደ አካሄዳችን በእኛ ላይ ቅጣትን ማምጣቱ ትክክለኛ ነው’ አሉ።”


跟着我们:

广告


广告