Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በኦሆላና በኦሆሊባ ላይ ፍርድ ለመስጠት ተዘጋጅተሃልን? ያደረጉትን አጸያፊ ነገር ግለጥላቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ጌታ እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሆላና በኦሆሊባ ትፈርዳለህን? ርኩሰታቸውን ንገራቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ሐላ​ንና ሐሊ​ባን ተፋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? ኃጢአታቸውንም ታስታውቃቸዋለህን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:36
15 交叉引用  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።


እነሆ መንቀልና ማፍረስ፥ ማጥፋትና መገለባበጥ፥ ማነጽና መትከል እንድትችል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ።”


ኤርምያስ ሆይ፥ እነርሱ በሚጨነቁበት ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ ስለማልሰማቸው ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ስለ እነርሱም ልመናና ምልጃ አታቅርብ።”


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ “ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤


የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።


“የሰው ልጅ ሆይ! ኢየሩሳሌም ያደረገችው ነገር ምን ያኽል አጸያፊ እንደ ሆነ አስታውቃት፤


“የሰው ልጅ ሆይ! በእነዚህ ሰዎች ላይ ትፈርድባቸዋለህን? ትፈርድባቸዋለህን? እንግዲያውስ አባቶቻቸው ያደረጉትን አጸያፊ ነገር እንዲያውቁ አድርጋቸው።


“የሰው ልጅ ሆይ! በነፍሰ ገዳዮች የተሞላችውን ከተማ ልትፈርድባት ተዘጋጅተሃልን? እንግዲያውስ የፈጸመቻቸውን አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ገልጠህ አሳያት።


ከእነርሱም ታላቂቱ ኦሆላ ትባል ነበር፤ እርስዋም ሰማርያ ነች፤ ታናሽቱ ደግሞ ኦሆሊባ ትባል ነበር እርስዋም ኢየሩሳሌም ነች፤ እኔ ሁለቱንም አግብቼ ልጆች ወለዱልኝ።


ልጆቼ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ እናታችሁ ሚስቴ ስላልሆነችና እኔም ባልዋ ስላልሆንኩ የዝሙት አመለካከትዋንና አመንዝራነትዋን እንድታስወግድ ውቀስዋት።


跟着我们:

广告


广告