ሕዝቅኤል 23:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ከእኅትሽ ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ እርሱም ትልቅና ጥልቀት ያለው ነው፤ ሰው ሁሉ መቀለጃና ማፌዣ ያደርግሻል፤ ጽዋውም ብዙ የሚይዝ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣ የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ ትጠግቢአለሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥልቅና ሰፊ የሆነውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የጠለቀውንና የሰፋውን፥ ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙ መጠጥን በሚጠጡ ሰዎችም ዘንድ መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፥ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ። 参见章节 |