Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ባቢሎናውያንም ከእርስዋ ጋር ለማመንዘር መጡ፤ ብዙ ጊዜ ስላረከሱአት በመጨረሻ ሁሉንም በመጸየፍ ጠላቻቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ባቢሎናውያንም መጥተው ወደ ፍቅር መኝታዋ ገቡ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት፤ እርሷም በእነርሱ ከረከሰች በኋላ ጠልታቸው ከእነርሱ ዘወር አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የባቢሎንም ልጆች ወደ እርሷ፥ ወደ ፍቅር አልጋ ገቡ፥ በዝሙታቸውም አረከሱአት፤ እርሷም በእነርሱ ረከሰች ነፍስዋም ከእነርሱ ተለየች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የባ​ቢ​ሎ​ንም ልጆች ወደ እር​ስዋ መጥ​ተው በመ​ኝ​ታዋ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኙ፤ በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውም አረ​ከ​ሱ​አት፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ረከ​ሰች፤ ነፍ​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ተለ​የች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ፍቅር ወዳለበት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት፥ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች ነፍስዋም ከእነርሱ ተለየች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:17
8 交叉引用  

በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር።


በዚያ እግዚአብሔር የሕዝቡን ቋንቋ ስለ ደበላለቀና እነርሱን በዓለም ዙሪያ ስለ በተናቸው የከተማውም ስም “ባቢሎን” ተባለ።


በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።


ከዚያም በኋላ አምኖን እጅግ አድርጎ ጠላት፤ እንዲያውም ቀድሞ ካፈቀራት ይበልጥ አሁን በእርስዋ ላይ ያለው ጥላቻ ስለ ባሰ “ከዚህ ውጪልኝ!” አላት።


ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።


በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የተደሰትሽባቸውን ማለት የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ ተጋልጠሽ ዕርቃንሽን ያዩ ዘንድ ከአካባቢው ሰብስቤ አንቺን በፊታቸው አራቊትሻለሁ።


“አሁንም ኦሆሊባ ሆይ! እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምልሽ ይህ ነው፤ እነዚያን ወዳጆችሽን ተጸይፈሻቸዋል፤ ነገር ግን እነርሱ በአንቺ እንዲነሡ አደርጋለሁ፤ እንዲከቡሽም ወደዚህ አመጣቸዋለሁ።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “በጥላቻ ለምትጸየፊያቸው ሕዝቦች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤


跟着我们:

广告


广告