Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱም ልብስዋን ገፈው እርቃንዋን አስቀሩአት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋን በምርኮ ያዙ፤ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉአት፤ ፍርድም በእርስዋ ላይ ተግባራዊ ሆነ፤ ሴቶች ሁሉ ስለ ገጠማት መጥፎ ዕድል አሉባልታ ማሰማት ጀመሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ገለጡ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ዋ​ንም ማር​ከው ወሰዱ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋና በሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ላይ በቀ​ልን ስላ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው በሴ​ቶች መካ​ከል መተ​ረቻ ሆነች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፥ ፍርድንም ስላደረጉባት በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 23:10
8 交叉引用  

ለጥፋት የተዳረግሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ቀይ ልብስ የለበስሽበት ምክንያት ምንድን ነው? ጌጣጌጥ ማድረግሽና ዐይንሽንስ መኳልሽ ለምንድነው? ውሽሞችሽ ጠልተውሽ ሊገድሉሽ ስለሚፈልጉ ውበትሽን የምትንከባከቢው በከንቱ ነው።


እርቃንዋን ወደ አደባባይ በመውጣት አመንዝራነትዋ በሰው ሁሉ ዘንድ እንዲጋለጥ አደረገች፤ እኔም እኅትዋን የተጸየፍኩትን ያኽል እርስዋንም ተጸየፍኳት።


አንቺን ከመጥላታቸው የተነሣ የደከምሽበትን ሁሉ ይወስዱብሻል፤ እርቃንሽንም አስቀርተው እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተ ሥጋሽ እንዲጋለጥ ያደርጋሉ፤ የተቃጠለ ፍትወትሽና ዘማዊነትሽ፥ ይህ ሁሉ እንዲደርስብሽ አድርጎአል፤ ለሕዝቦች ሁሉ የፍትወት መጠቀሚያ ዘማዊት ሆነሽ በጣዖቶቻቸው ራስሽን አረከስሽ።


እናንተ ሁለት እኅትማማቾች እንዳመነዘራችሁ ሁሉ ሴቶች ከእንግዲህ ወዲህ እንዳያመነዝሩ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከምድሪቱ ሁሉ ላይ የሴሰኝነት ስድነት እንዲወገድ አደርጋለሁ።


በፍቅረኞችዋም ፊት እርቃንዋን አስቀራታለሁ፤ ከእጄም የሚያድናት የለም።


ባትመለስ ግን እንደ ተወለደችበት ቀን እርቃንዋን አስቀራታለሁ፤ እንደ ደረቀ ባዶ ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።


跟着我们:

广告


广告