Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እነርሱም በእርስዋ ውስጥ ይቀልጣሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር የቊጣዬን ኀይል እንዳወረድኩባቸው ያውቃሉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ብር በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፣ እናንተም በከተማዪቱ ውስጥ ትቀልጣላችሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም ጌታ መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ብርም በከ​ውር ውስጥ እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ በው​ስ​ጥዋ ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቴን እን​ዳ​ፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ብርም በከውር ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጡዋ ትቀልጣላችሁ፥ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:22
10 交叉引用  

ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ በእርግጥ በሥልጣኔ፥ በሙሉ ኀይሌና በቊጣዬ በእናንተ ላይ እነግሣለሁ።


ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።


ሌሎች አሕዛብ ያዋርዱሻል፤ ስለዚህም አንቺ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂያለሽ።”


አዎ በኢየሩሳሌም እሰበስባቸዋለሁ፤ እሳትንም አቀጣጥዬ በቊጣዬ አቀልጣቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንደገና እንዲህ አለኝ፦


ስለዚህ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በኀይለኛ ቊጣዬም አጠፋቸዋለሁ፤ በደላቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


በሀገሪቱ ላይ ስለ ፈጸሙት ግድያና በጣዖት አምልኮም ምድሪቱን በማርከሳቸው ምክንያት ኀይለኛ ቊጣዬን አወረድኩባቸው።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ መሪዎች የእስራኤልን ድንበር እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ ስለዚህ እኔ ቊጣዬን እንደ ጐርፍ ውሃ አወርድባቸዋለሁ።


ከዚህ በኋላ ሰባቱን መላእክት “ሂዱ! የእግዚአብሔርን ቊጣ የያዙትን ሰባቱን ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ!” የሚል ከፍ ያለ ድምፅ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告