Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አዎ በኢየሩሳሌም እሰበስባቸዋለሁ፤ እሳትንም አቀጣጥዬ በቊጣዬ አቀልጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሰብስቤአችሁ የቍጣዬን እሳት በእስትንፋሴ አነድድባችኋለሁ፤ እናንተም በዚያ ውስጥ ቀልጣችሁ ትቀራላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ቍጣዬን በላያችሁ እንዳፈሰስሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እሰበስባችሁአለሁ፥ የመዓቴንም እሳት አነድባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በላ​ያ​ችሁ የመ​ዓ​ቴን እሳት አነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትቀ​ል​ጣ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:21
20 交叉引用  

እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤


ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።


በምትገለጥበት ጊዜ ከምድጃ እንደሚወጣ የእሳት ነበልባል ታቃጥላቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በቊጣው ወላፈን ይለበልባቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል።


አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው።


ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ!


ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።


እሳት ደረቁን እንጨት በሚያጋይ ጊዜ ፍሙ የተጣደውን ውሃ እንደሚያፍለቀልቀው፥ ሕዝቦችም በአንተ መገለጥ እንዲንቀጠቀጡ ወርደህ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ አድርግ!


በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።


“ገበሬ ሰብሉን እንደሚሰበስብ ሕዝቤን ልሰበስብ ፈለግኹ፤ እነርሱ ግን ዘለላ እንደሌለው የወይን ተክል ፍሬ አልባ እንደ ሆነ የበለስ ዛፍና ቅጠሉ እንደ ረገፈ ተክል ሆኑብኝ፤ በዚህ ምክንያት የሰጠኋቸውን ምድር ባዕዳን እንዲወስዱባቸው አደረግሁ።”


ከዚህም የተነሣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን ለማጥራት እንደ ብረት እፈትናቸዋለሁ፤ ሕዝቤ ክፉ ነገር ስለ ፈጸሙ ይህን ከማድረግ በቀር ሌላ ምን አደርጋቸዋለሁ?


የቊጣዬ ኀይል እንደ ተቀጣጠለ እሳት በእናንተ ላይ ይወርዳል፤ የማጥፋት ልምድ ላላቸው ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤


በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።


እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።


እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።


በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ነው፤ ቀናተኛ አምላክ ነው።


跟着我们:

广告


广告