Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ዝርፊያችሁንና ነፍስ መግደላችሁን በመቃወም በእናንተ ላይ እጄን አነሣለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ያለ አግባብ ባገኘሽው ጥቅምና በመካከልሽ ባፈሰስሽው ደም ላይ እጄን አጨበጭባለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ ያለ አግባብ በአገኘሽው ትርፍና በመካከልሽ በፈሰሰው ደም ላይ እጄን አጨበጨብሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ስለ​ዚህ እነሆ አንቺ ባደ​ረ​ግ​ሽው ሥራ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ሽም በነ​በ​ረው ደም ላይ በእጄ አጨ​በ​ጨ​ብሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ፥ እነሆ፥ አንቺ ባደረግሽው ስስት በመካከልሽም በነበረው ደም ላይ እጄን አጨበጨብሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 22:13
16 交叉引用  

በአራጣ በማበደርና ሰዎችን በመበዝበዝ የሚከብር ሰው ሀብቱ ሁሉ ለድኾች ልግሥና ለሚያደርግ ሰው ይተላለፋል።


በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥


“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በቊጣ አማታው፤ ሰይፉም በመደጋገም ተወዛውዞ እየዞረም የሚገድል፥ የሚያሸብርና የሚያርድ ሰይፍ ነው፤


እኔም በቊጣ እጄን አማታለሁ፤ ኀይለኛ ቊጣዬም ይበርዳል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ሰይፉን ይዞ የሚመጣባቸውን ሁለቱን መንገዶች ምልክት አድርግባቸው፤ የሁለቱም መነሻቸው አንዲት አገር ናት፤ ሁለቱ መንገዶች በሚገናኙበት መስቀለኛ ስፍራ ወደ ከተማ የሚያመራውን ምልክት ትከል።


ባለ ሥልጣኖቹ፥ የገደሉትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኲላዎች ናቸው፤ ያለ አግባብ ለመበልጸግ ሰውን ይገድላሉ፤


ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነዚህ ሕዝቦች መልካም ነገር ማድረግን አያውቁም፤ በዐመፅና በግፍ በተወሰደ ንብረት ምሽጋቸውን ይሞላሉ፤


ባላቅ በቊጣ እጆቹን ጨብጦ በለዓምን እንዲህ አለው፤ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠርቼህ ነበር፤ አንተ ግን ስትመርቃቸው ይኸው ሦስተኛ ጊዜህ ነው።


በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።


跟着我们:

广告


广告