Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም መልሰህ በተቀደሱ ቦታዎችዋ ላይና በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙር፤ በመቅደሱ ላይ ቃል ተናገር፤ በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተንብይ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አድርግ፥ ስለ መቅደሶችም ስበክ፤ በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተናገር

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ፊት​ህን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አቅና፤ ወደ መቅ​ደ​ሶ​ችም ተመ​ል​ከት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር ላይ ትን​ቢት ተና​ገር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና ወደ መቅደሶችም ተናገር በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:2
21 交叉引用  

ንግግሬ ያረካቸው ስለ ነበር፥ ከእኔ ንግግር በኋላ የሚናገር ሰው አልነበረም።


አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤


ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእነርሱ ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ ትንቢት ተናገር።”


“የሰው ልጅ ሆይ! ወደ ደቡብ ፊትህን አዙረህ በደቡብ ላይ ተናገር፤ በደቡብ በኩል ባለው ጫካ ላይም ትንቢት ተናገርበት።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ ወዮላት! ማገዶውን እኔ ራሴ አብዝቼ እጨምራለሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ዐሞን ምድር አዙረህ በዐሞናውያን ላይ ትንቢት ተናገር።


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሲዶና መልሰህ በእርስዋ ላይ ትንቢት ተናገር፤


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን በግብጽ ንጉሥ ላይ መልሰህ በእርሱና በግብጽ ሕዝብ ላይ ትንቢት ተናገር።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ያዳምጡ ዘንድ ንገራቸው፤


“የሰው ልጅ ሆይ! በማጎግ ምድር የሚገኙት የሜሼክና የቱባል ሕዝቦች ገዢ የሆነውን ጎግን በመቃወም ትንቢት ተናገርበት፤


የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል እንደ ቅጽር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ ከተማይቱ አቅና፤ የተከበበችም ትምሰል፤ የምትከባትም አንተው ነህ፤ ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ምልክት ይሆናል።


“ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ትኲር ብለህ ተመልከት፤ እጅህንም አንሥተህ የማስጠንቀቂያ ትንቢት በእርስዋ ላይ ተናገር።


“የሰው ልጅ ሆይ! ወደ እስራኤል ተራራዎች ተመልከት፤ በእነርሱም ላይ ትንቢት ተናገር።


አሁንም እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስማ፤ አንተ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ የይስሐቅ ዘሮች የሆኑትንም የእስራኤልን ሕዝብ አትስበክ’ ብለህ ከልክለኸኛል።


“አንድ ሰው ባዶ ቃላትን በመደርደር ስለ ወይንና ስለ ጠንካራ መጠጥ አስተምራችኋለሁ ቢላችሁ የዚህ ሕዝብ ነቢይ የሚሆነው እርሱ ነው።


የእነርሱ ነቢያት “ትንቢት አትናገር፤ እንደዚህ ያለው ውርደት የማይደርስብን ስለ ሆነ ስለ ነዚህ ጉዳዮች ትንቢት አትናገር” ይሉኛል።


የወንጌልን ምሥጢር ያለ ፍርሀት እንድገልጥ በምናገርበት ጊዜ አስፈላጊውን ቃል እንዲሰጠኝ ለእኔም ጸልዩልኝ።


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥


跟着我们:

广告


广告