Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ሰይፉን ይዞ የሚመጣባቸውን ሁለቱን መንገዶች ምልክት አድርግባቸው፤ የሁለቱም መነሻቸው አንዲት አገር ናት፤ ሁለቱ መንገዶች በሚገናኙበት መስቀለኛ ስፍራ ወደ ከተማ የሚያመራውን ምልክት ትከል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን የሁለት መንገዶች ካርታ ንደፍ፤ መንገዶቹም ከአንድ አገር የሚነሡ ናቸው፤ መንገዱ ወደ ከተማው በሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አቁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣበትን ሁለት መንገዶችን አድርግ፥ ሁለቱም ከአንዲት ምድር ይውጡ፥ ምልክትም አድርግ፥ በከተማይቱ መንገድ ራስ ላይ አድርገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሰይፍ የም​ት​ገ​ባ​ባ​ቸው ሁለት መን​ገ​ዶ​ችን አድ​ርግ፤ ሁለ​ቱም ከአ​ን​ዲት ምድር ይውጡ፤ ምል​ክ​ት​ንም አድ​ርግ፤ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መን​ገድ ራስ ላይም አድ​ር​ገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣ ዘንድ ሁለት መንገዶችን አድርግ፥ ሁለቱም ከአንዲት ምድር ይውጡ፥ ምልክትም አድርግ፥ በከተማይቱ መንገድ ራስ ላይ አድርገው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:19
9 交叉引用  

እነሆ መንቀልና ማፍረስ፥ ማጥፋትና መገለባበጥ፥ ማነጽና መትከል እንድትችል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ።”


ሰይፉ ተወልውሎ በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቶአል፤ ለገዳዩ ይሰጥ ዘንድ ተስሎና ተወልውሎ ተዘጋጅቶአል።


ሕዝቤ በፍርሃት በመሞላት ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እንደ መብረቅ በሚያብለጨልጭ፥ ለመግደያ የተዘጋጀውን ሰይፍ፥ በየበራፋቸው አድርጌአለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦


“ዝርፊያችሁንና ነፍስ መግደላችሁን በመቃወም በእናንተ ላይ እጄን አነሣለሁ።


ባቢሎናውያንንና ከለዳውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ የፈቆድን፥ የሾዐንና የቆዐንን ወንዶች እንዲሁም አሦራውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ ወጣትነት ያላቸው፥ መልከ ቀና የሆኑ መሳፍንትና የጦር መኰንኖች፥ ታላላቅ ባለሥልጣኖችና ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው እነዚህ ሁሉ በፈረስ ተቀምጠው ይመጣሉ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር ስለሚመቱ ስለ እስራኤላውያን ክፉ ርኲሰት ሁሉ ወዮ! እያላችሁ እጆቻችሁን እያማታችሁና በእግሮቻችሁ እየረገጣችሁ ሐዘናችሁን ግለጡ!


跟着我们:

广告


广告