Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እኔም በቊጣ እጄን አማታለሁ፤ ኀይለኛ ቊጣዬም ይበርዳል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤ ቍጣዬም ይበርዳል፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እኔም ደግሞ መዳፌን በመዳፌ እመታለሁ፥ ቁጣዬም ይበርዳል፥ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እኔ ደግሞ እጄን በእጄ ላይ አጨ​በ​ጭ​ባ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም እል​ካ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እኔ ደግሞ በእጄ አጨበጭባለሁ መዓቴንም እጨርሳለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:17
13 交叉引用  

ስለዚህ፥ የእስራኤል ኀይል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጠላቶቼ ላይ ኀይለኛ ቊጣዬን አውርጄ ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ።


ከአንተ ርቀን ብንሄድም እንኳ አሁን ንስሓ ገብተናል፤ በዕፍረትና በጸጸት ራሳችንን ዝቅ አድርገን ደረታችንን እንመታለን፤ በወጣትነት ዘመናችን ለፈጸምነው ኃጢአት ራሳችንን እንወቅሳለን።’


ወደ እርሻ አትውጡ፤ በመንገድ ላይም አትዘዋወሩ፤ በየአቅጣጫው ሽብር ስለ ሆነ ከጠላት ሰይፍ ተጠንቀቁ።”


ስለዚህ በአንቺ ላይ ያለኝ ቊጣ ያበቃል፤ ቅናቴም ከአንቺ ይርቃል፤ በአንቺ ላይ የነበረው ቊጣዬም ይበርዳል፤ ዳግመኛም አልቈጣም።


“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በቊጣ አማታው፤ ሰይፉም በመደጋገም ተወዛውዞ እየዞረም የሚገድል፥ የሚያሸብርና የሚያርድ ሰይፍ ነው፤


አንተ ስለታም ሰይፍ! ስለትህ በዞረበት በቀኝና በግራ ቈራርጥ!


እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦


“ዝርፊያችሁንና ነፍስ መግደላችሁን በመቃወም በእናንተ ላይ እጄን አነሣለሁ።


መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


“ቊጣዬ በእርሱ ላይ ይፈጸማል ኀይለኛ ቊጣዬንም በእነርሱ ላይ አውርጄ እረካለሁ ይህንንም ቊጣዬን በእነርሱ ላይ ባወረድኩ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅናቴ የተናገርኩ መሆኔን ያውቃሉ።


ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ ሰሜን አገሮች የሄዱት ፈረሶች የእግዚአብሔርን ቊጣ እንዲበርድ አደረጉ” ሲል ወደ እኔ ጮኸ።


ባላቅ በቊጣ እጆቹን ጨብጦ በለዓምን እንዲህ አለው፤ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠርቼህ ነበር፤ አንተ ግን ስትመርቃቸው ይኸው ሦስተኛ ጊዜህ ነው።


እግዚአብሔር እናንተን ለማበልጸግና ቊጥራችሁንም ለማብዛት እንደ ወደደው ሁሉ እንደገናም እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስ ደስ ይለዋል። ከዚህች ከምትወርሱአት ምድር ተነቃቅላችሁ ትጠፋላችሁ።


跟着我们:

广告


广告