Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሰይፉ ተወልውሎ በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቶአል፤ ለገዳዩ ይሰጥ ዘንድ ተስሎና ተወልውሎ ተዘጋጅቶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘በእጁ እንዲያዝ፣ ሰይፉ ሊወለወል ተሰጥቷል፤ ገዳዩ በእጁ እንዲጨብጠው፣ ተስሏል፤ ተወልውሏል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሰይፉ እንዲወለወል፥ በእጅም እንዲያዝ ተሰጠ፤ በገዳዩ እጅ እንዲቀመጥ ተሳለ፥ ተወለወለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በእ​ጁም ይይ​ዛት ዘንድ ለአ​ር​በኛ ተሰ​ጠች፤ ሰይፍ በገ​ዳይ እጅ እን​ድ​ት​ሰጥ ተሳ​ለ​ችና ተዘ​ጋ​ጀች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በእጅም እንዲያዝ ለመሰንገል ተሰጠ፥ ሰይፍ በገዳይ እጅ እንዲሰጥ ተሳለና ተሰነገለ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:11
8 交叉引用  

መርዶክዮስም ስለ ተደረገው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከዚህም በኋላ ማቅ ለብሶና በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ በመረረ ሁኔታ በማልቀስ ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገባ።


ስለ ሞቱት ሕዝቦቼ በመረረ ሁኔታ አለቅስላቸው ዘንድ ተዉኝ፤ አታጽናኑኝ።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ።


‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ለመግደያ ተስሎአል፤ እንደ መብረቅ ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል፤ ሕዝቤ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያና ቅጣት ሁሉ ችላ ስላሉ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደስታ አይኖርም።


የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤ ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው። እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤ ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።


“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ሰይፉን ይዞ የሚመጣባቸውን ሁለቱን መንገዶች ምልክት አድርግባቸው፤ የሁለቱም መነሻቸው አንዲት አገር ናት፤ ሁለቱ መንገዶች በሚገናኙበት መስቀለኛ ስፍራ ወደ ከተማ የሚያመራውን ምልክት ትከል።


跟着我们:

广告


广告