Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለመግደያ ተስሎአል፤ እንደ መብረቅ ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል፤ ሕዝቤ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያና ቅጣት ሁሉ ችላ ስላሉ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደስታ አይኖርም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የተሳለው ሊገድል፣ የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው! “ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲገድል ተስሎአል እንዲያብረቀርቅም ተወልውሏል፥ እኛስ ደስ ይለናልን? የልጄን በትር እንደ ማንኛውም ዛፍ ንቆታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ወግ​ተሽ ትገ​ድሊ ዘንድ፥ ታብ​ረ​ቀ​ር​ቂም ዘንድ ተሳዪ፤ ትገ​ድ​ሊም ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ሁሉ ትጥዪ ዘንድ ጨክኚ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይገድል ዘንድ ተስሎአል ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል፥ እኛስ ደስ ይለናልን? የልጄን በትር እንደ ዛፍ ሁሉ ንቆታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 21:10
23 交叉引用  

እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ስሕተት በሚፈጽምበትም ጊዜ አባት ልጁን እንደሚቀጣ እቀጣዋለሁ፤


በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለመጨፈርም ጊዜ አለው።


እግዚአብሔር ያቀደውን ተግባራዊ አድርጎ እስኪፈጽም ድረስ ቊጣው ከቶ አይገታም፤ ወደ ፊት ሕዝቡ ይህን ሁሉ በግልጥ ይረዱታል።


ፈረሶቻችሁን ለጒማችሁ ርካብ ረግጣችሁ ውጡ፤ የራስ ቊር ደፍታችሁ ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ የጦር ልብሳችሁንም ልበሱ።


ለደቡብም ጫካ እኔ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ የሚለውን ስማ ብለህ ንገረው፤ ‘ተመልከት! እነሆ እኔ በውስጥህ እሳትን በማቀጣጠል ላይ ነኝ፤ ይህም እሳት ለምለሙንም ሆነ ደረቁን ሳይመርጥ ዛፎችን ሁሉ ያቃጥላል፤ እሳቱንም ሊያጠፋው የሚችል አይኖርም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ይዛመታል፤ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል።


ሰይፉ ተወልውሎ በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቶአል፤ ለገዳዩ ይሰጥ ዘንድ ተስሎና ተወልውሎ ተዘጋጅቶአል።


ከመካከልሽም ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ለማጥፋት ከደቡብ እስከ ሰሜን ባሉት ሁሉ ላይ ሰይፌ ከሰገባው ይመዘዛል።


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ፈረሰኞች ወደፊት እየገፉ የሚያብረቀርቅ ሰይፋቸውንና የሚያብለጨልጭ ጦራቸውን ያነሣሉ፤ ብዙ ሰዎች ስለ ተገደሉ ሬሳዎች ተከምረዋል፤ ከሬሳውም ብዛት የተነሣ በዚያ የሚያልፍ ሰው ሁሉ ይደናቀፋል።


እንደ ፍላጻ ከሚወረወረውና እንደ ጦር ከሚያንጸባርቀው መብረቅህ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ።


‘በብረትም በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ቀጥቅጦ ያደቃቸዋል፤’ ይህም ሥልጣን እኔ ከአባቴ እንደ ተቀበልኩት ዐይነት ነው፤


跟着我们:

广告


广告