Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 እኔ እግዚአብሔር የደቡብን ጫካ በእሳት እንዳያያዝኩትና ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል ሁሉም ይመለከታሉ።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ሰው ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ያያል፤ የሚያጠፋውም የለም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 እኔ ጌታ እንዳነደድሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እርሱም አይጠፋም በለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ነ​ደ​ድ​ሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እር​ሱም አይ​ጠ​ፋም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 እኔም እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እርሱም አይጠፋም በለው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:48
11 交叉引用  

አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።


ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”


ነገር ግን ስላደረግሽው ነገር ሁሉ እኔ እቀጣሻለሁ፤ ቤተ መንግሥትሽ በእሳት እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ያም እሳት በዙሪያው የሚገኘውን ነገር ሁሉ ያጋያል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ስለዚህ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሴ በተሠራበት በዚህ ቦታ ላይ ብርቱ ቊጣዬን አፈሳለሁ፤ በሰዎችና በእንስሶች ላይ፥ በዛፎችና በሰብልም ሁሉ ላይ ሳይቀር አፈሰዋለሁ፤ ቊጣዬ ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል እሳት ይሆናል።


ከወይን ተክሉ ግንድ እሳት ወጣ፤ ቅርንጫፎቹንና ፍሬውን ሁሉ እሳት በላው፤ ቅርንጫፎቹ ዳግመኛ ብርቱ አይሆኑምና በትረ መንግሥት መሆንም አይችሉም። እንግዲህ በመደጋገም የሚደረደረው ሙሾ ይህ ነው። እርሱም ለለቅሶ ያገለግላል።


በእሳት ትጠፋላችሁ፤ ደማችሁ በገዛ አገራችሁ ላይ ይፈስሳል፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳችሁ አይኖርም፤’ ” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።


跟着我们:

广告


广告