ሕዝቅኤል 20:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም47 ለደቡብም ጫካ እኔ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ የሚለውን ስማ ብለህ ንገረው፤ ‘ተመልከት! እነሆ እኔ በውስጥህ እሳትን በማቀጣጠል ላይ ነኝ፤ ይህም እሳት ለምለሙንም ሆነ ደረቁን ሳይመርጥ ዛፎችን ሁሉ ያቃጥላል፤ እሳቱንም ሊያጠፋው የሚችል አይኖርም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ይዛመታል፤ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም47 ለደቡቡ ደን እንዲህ በል፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በአንተ ላይ እሳት ልለኵስ ነው፤ እሳቱ የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍህን ሁሉ ይበላል፤ የሚንቦገቦገው ነበልባሉም አይጠፋም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት ሁሉ ይለበልባል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)47 ለደቡብም ዱር፦ የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)47 ለናጌብም ዱር እንዲህ በለው፦ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንተ ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፤ የሚቃጠለውም ነበልባል አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)47 ለደቡብም ዱር፦ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል፥ የሚቃጠል ነበልባል አይጠፋም፥ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃጠልበታል። 参见章节 |