Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ለእነርሱ እንደምሰጣቸው ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር አመጣኋቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱ ከፍተኛ ኰረብቶችንና ለምለም ዛፎችን ባዩ ጊዜ በሁሉም ላይ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በሚቃጠል መሥዋዕታቸው፥ መዓዛው በሚጣፍጥ ዕጣናቸውና ለመሥዋዕትም በሚያፈሱት የመጠጥ ቊርባናቸው አስቈጡኝ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ባስገባኋቸው ጊዜ፣ ከፍ ያለውን ኰረብታ ሁሉና የለመለመውን ዛፍ ሁሉ ተመለከቱ፤ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ ቍርባናቸውን በማቅረብ ቍጣዬን አነሣሡ፤ መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣናቸውን ዐጠኑ፤ የመጠጥ ቍርባናቸውንም አፈሰሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቆጣኝን ቁርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቁርባናቸውን አፈሰሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:28
24 交叉引用  

ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤


በኰረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ ዐምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፤


እግዚአብሔር ለጣዖት እንዳይሰግዱ ያዘዛቸውንም ሕግ ሁሉ አፈረሱ።


እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተራሮች ላይ መሥዋዕት በማቅረባቸውና ስሜን ባለማክበራቸው ስለ እነርሱና ስለ አባቶቻቸው በደል ዋጋቸውን በሙሉ እከፍላቸዋለሁ።”


የኢየሩሳሌም ሕዝብና የይሁዳ ነገሥታት የሚኖሩባቸው ቤቶች፥ እንዲሁም በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ዕጣን የሚታጠንባቸውና ለባዕዳን አማልክትም የወይን ጠጅ የሚፈስባቸው ቤቶች ሁሉ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።”


የምታስገኘውን ሰብልና ሌሎችን መልካም ነገሮች ሁሉ አግኝተው እንዲደሰቱ ለም ወደ ሆነች ምድር አገባኋቸው፤ እነርሱ ግን ምድሬን አበላሹ፤ የሰጠኋቸውን አገር አረከሱ።


ኢዮስያስ በነገሠበት ዘመን እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “እምነት አጒዳይ የሆነችው እስራኤል ምን እንዳደረገች አይተሃልን? እርስዋ ከእኔ ተለይታ በየከፍተኛው ተራራና በየለመለመው ዛፍ ሥር ጣዖትን በማምለክ ርኲሰትን ፈጽማለች።


የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከክፉ አድራጎት በስተቀር ምንም ያደረጉት መልካም ነገር የለም። በተለየም የእስራኤል ሕዝብ በእጃቸው በሠሩት ጣዖት እኔን ከማስቈጣት በቀር ምንም የሠሩት ነገር የለም።


ምርጥ የሆነ ዱቄት የወይራ ዘይትና ማር. ምግብ እንዲሆንሽ ሰጥቼሽ ነበር፤ አንቺ ግን ጣዖቶችን ለማስደሰት መልካም መዓዛ ያለው መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሽ፤” ይህም ተደርጓል፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


መድረክ እየሠራሽ በየ አደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ አዘጋጀሽ።


ከዚህም በላይ ከዓለም ምድር ሁሉ ውብ የሆነችውንና በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እሰጣችኋለሁ ብዬ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በበረሓ እያሉ ወደዚያ እንደማላስገባቸው አረጋግጬ ነገርኳቸው።


እኔም ‘እነዚህ የምትሄዱባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ምንድን ናቸው?’ ብዬ ጠየቅኋቸው፤ እስከ ዛሬ ድረስ ‘ከፍተኛ ቦታዎች’ ተብለው ይጠራሉ።


ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው።


ሬሳዎች በጣዖቶችና በመሠዊያዎች ዙሪያ ይከመራሉ፤ በከፍተኛ ኰረብቶችና በተራሮች ጫፍ ላይ፥ እንዲሁም በየለምለሙ ዛፍና በየትልልቁ ወርካ ሥር ለጣዖቶቻቸው መልካም ሽታ ባቀረቡባቸው ስፍራዎች ሁሉ ሬሳዎች ይወድቃሉ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።


“ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል።


“እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ደርሶአል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ያደረገላችሁን መልካም ነገር ሁሉ ከእናንተ እያንዳንዱ በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ያውቃል፤ እርሱ ከሰጣችሁ ተስፋ አንድም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።


跟着我们:

广告


广告