Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ነገር ግን እስራኤላውያንን ከግብጽ ማውጣቴን በተመለከቱ ሕዝቦች ዘንድ ስሜ እንዳይነቀፍ ይህን አላደረግሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነገር ግን ከግብጽ ሳወጣቸው ባዩ አሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ እጄን ሰበሰብሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ የሚ​በ​ል​ጠው ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ አደ​ረ​ግሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:22
14 交叉引用  

ይኸውም የቅጣት ክንድህን ከእኔ ላይ አንሣ፤ አስፈሪ በሆነው ግርማህ አታስደንግጠኝ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ እኛ ሳይሆን ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ ታማኝነትህ ስምህን አክብረው።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ስምህ ክብር እጅግ የበዛውን ኃጢአቴን ይቅር በልልኝ።


ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።


የተስፋ ቃልህን ሁሉ በማሰብ እኛን አትናቀን፤ ግርማህ የሚገለጥበት የክብር ዙፋንህ መኖሪያ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን አታዋርዳት፤ ከእኛም ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስብ።


ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።


እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ።


ነገር ግን እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርቼ ሳወጣ በተመለከቱኝ ሕዝቦች ፊት ስሜ እንዳይነቀፍ ይህን ሁሉ አላደረግሁም።


ይህም ሆኖ ስለ ራራሁላቸው አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልጨረስኳቸውም።


ነገር ግን አብረዋቸው በሚኖሩት ሕዝቦች ፊት ከግብጽ እንደማወጣቸው ለእስራኤላውያን ቃል ገብቼ ነበር፤ ስለዚህ ስሜ እንዳይነቀፍ እነርሱን ከግብጽ እንዲወጡ አድርጌአለሁ።


አምላክ ሆይ! ጸሎቴንና ልመናዬን ስማ፤ ስለ ስምህ ስትል ለፈረሰው ቤተ መቅደስህ ራራ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።”


跟着我们:

广告


广告