Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ነገር ግን ልጆቻቸው በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚፈጽመው ሁሉ ሕይወት የሚያስገኝለትን ሕጌን አፈረሱ፤ ሕጎቼንም አልጠበቁም፤ ሰንበትንም አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ሳሉ የቊጣዬን ኀይል በእነርሱ ላይ በማውረድ ሁሉንም ላጠፋቸው አስቤ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ ‘ልጆቻቸው ግን በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልተከተሉም፤ ሕጌን ለመጠበቅ አልተጉም፤ ሰንበቴንም አረከሱ። እኔም በምድረ በዳ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም አወርድባቸዋለሁ ብዬ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልጆች ግን ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጓትም በሥርዓቴም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ ቁጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ልጆች ግን ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጓትም በሥርዓቴም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም አረከሱ፥ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ ቍጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለህ አልሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:21
22 交叉引用  

“ሄዳችሁ ስለ እኔና እንዲሁም በእስራኤልና በይሁዳ ስለ ቀረው ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ በዚህ መጽሐፍ ስላለውም ትምህርት አረጋግጡ፤ የቀድሞ አባቶቻችን ለእግዚአብሔር ቃል ባለመታዘዛቸውና ይህ መጽሐፍ አድርጉ የሚላቸውን ሁሉ ባለመፈጸማቸው፥ እግዚአብሔር ቊጣውን በእኛ ላይ አውርዶአል።”


እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ ይህም ያደረጉት በደል ቊጣዬን አነሣሥቶአል፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተነሣሣው ቊጣዬም ይፈጸማል እንጂ አይበርድም፤


ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ ሕጉንም ለመፈጸም እምቢ አሉ።


ነገር ግን ወደዚህች ምድር መጥተው ከወረሱአት በኋላ ለቃልህ መታዘዝንና በአስተማርካቸው ሕግ ጸንተው መኖርን እምቢ አሉ፤ ያዘዝካቸውንም ነገር ሁሉ አልፈጸሙም፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ሁሉ ጥፋት አመጣህባቸው።


እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ገለጠ፤ የጽዮንን መሠረት የሚያጠፋ፥ የተቀጣጠለ እሳት የመሰለ መዓቱን አወረደ።


“በቅጥሩ ላይና ቅጥሩን ቀለም በቀቡበት ላይ ኀይለኛ ቊጣዬን አወርዳለሁ፤ ከዚያም በኋላ ቅጥሩም ሆነ ቅጥሩን ቀለም የቀቡት አይኖሩም እላችኋለሁ።


ለሚታዘዘው ሁሉ በሕይወት መኖር የሚችልበትን ሕጌን ሰጠኋቸው፤ ሥርዓቴንም አስተማርኳቸው፤


ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤


በግብጽ በረሓ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ፈረድኩ በእናንተም ላይ እፈርዳለሁ፤” ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።


ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።


የቊጣዬ ኀይል እንደ ተቀጣጠለ እሳት በእናንተ ላይ ይወርዳል፤ የማጥፋት ልምድ ላላቸው ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤


ለእኔ የተቀደሱ በሆኑ ነገሮች ላይ አክብሮት የላችሁም፤ ሰንበቴንም አረከሳችሁ።


“አሁን እኔ በቅርቡ ቊጣዬንና መዓቴን አወርድባችኋለሁ፤ እንዳካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ፤ በአጸያፊ ድርጊታችሁም ምክንያት እቀጣችኋለሁ።


“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።


በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!”


ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።


ለአርባ ዓመትም ያኽል በበረሓ ታገሣቸው


የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤


ከዚህ በኋላ ሰባቱን መላእክት “ሂዱ! የእግዚአብሔርን ቊጣ የያዙትን ሰባቱን ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ!” የሚል ከፍ ያለ ድምፅ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告