Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ ከእናንተ ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንላችሁ ዘንድ፥ እንዲሁም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ያስታውሳችሁ ዘንድ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆን ዘንድ ሰንበቴን የተቀደሰ ቀን አድርጉት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁም ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰንበታቴንም ቀድሱ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:20
13 交叉引用  

በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።


“የሰንበትን ቀን አክብር፤ ቀድሰውም፤


ይህን የሚያደርግ፥ አጥብቆ የሚይዘው፥ ሰንበትን ሳይሽር የሚጠብቅ፥ እጁንም ክፉ ነገር ከማድረግ የሚገታ ሰው የተባረከ ነው።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥


የቀድሞ አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጋችሁ አክብሩ እንጂ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ ከቤታችሁ አትውጡ፤ በሰንበት ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።


“‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።


ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”


የምቀድሳቸው እኔ መሆኔን ያውቁ ዘንድ ሰንበትን ማክበራቸው በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት እንዲሆን አደረግሁ።


የበኲር ልጆቻቸውን እስከ መሠዋት ድረስ ተቀባይነት የሌለውን መሥዋዕት በማቅረብ ራሳቸውን እንዲያረክሱ ተውኳቸው፤ ይህንንም ያደረግኹት እነርሱን መቀጣጫ የማደርጋቸው እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቁ ዘንድ ነው።


ለእኔ የተቀደሱ በሆኑ ነገሮች ላይ አክብሮት የላችሁም፤ ሰንበቴንም አረከሳችሁ።


ሕግን በሚመለከት አከራካሪ ነገር በሚነሣበት ጊዜ፥ ደንቡ በሚያዝዘው መሠረት ካህናቱ ይወስኑላቸው፤ በሕጌና ሥርዓቴ መሠረት በዓሎቼን፥ እንዲሁም ዕለተ ሰንበትን በመቀደስ ይጠብቁ።


跟着我们:

广告


广告