Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 20:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ዐመፀብኝ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሕጌንም ተላለፉ፤ ሰንበቴንም ፈጽሞ አረከሱ። እኔም መዓቴን ላፈስስባቸው፣ በምድረ በዳም ላጠፋቸው ወስኜ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 20:13
43 交叉引用  

ታዲያ ትእዛዜን የናቅኸው ስለምንድን ነው? ይህንንስ ክፉ ነገር ለምን አደረግህ? ኦርዮን በጦር ሜዳ አስገደልከው፤ ንጹሑን ሰው ዐሞናውያን እንዲገድሉት አደረግህ፤ ሚስቱንም ወሰድክ!


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዳልሆኑት እንደ ቀድሞ አባቶቻችሁና እንደ ወገኖቻችሁ እስራኤላውያን አትሁኑ፤ እንደምታውቁት እግዚአብሔር እነርሱን ለጥፋት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል፤


እኔም የአይሁድ መሪዎችን በመገሠጽ እንዲህ አልኳቸው፥ “የምታደርጉትን ክፉ ነገር ሁሉ ተመልከቱ! እነሆ ሰንበትን እያረከሳችኋት ነው፤


አሁንም እነሆ፥ በእነርሱ ላይ እጅግ ተቈጥቼ ላጠፋቸው ስለ ተዘጋጀሁ ተወኝ፤ አንተንም ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”


እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።


ምክሬን ናቃችሁ፤ ተግሣጼንም አልተቀበላችሁም።


መልካም ምክርን የሚንቅ ችግር ይደርስበታል፤ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ዋጋ ያገኝበታል።


ከባዕድ አገር መጥተው፥ ወደ እግዚአብሔር በመጠጋት እርሱን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን፥ የእርሱን ሰንበት ሳይሽሩ በማክበር ቃል ኪዳኑን የሚጠብቁትን ባዕዳንን እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦


ሆኖም እነርሱ የእርሱን ቅዱስ መንፈስ አሳዘኑ፤ ስለዚህ እሱ በእነርሱ ላይ ተነሥቶ ቀጣቸው።


እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ትኲረትም አልሰጡትም፤ በዚህ ፈንታ በእልኽና በክፋት የተሞላው ልባቸው የመራቸውን አደረጉ፤ ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ።


ለሚታዘዘው ሁሉ በሕይወት መኖር የሚችልበትን ሕጌን ሰጠኋቸው፤ ሥርዓቴንም አስተማርኳቸው፤


ነገር ግን እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርቼ ሳወጣ በተመለከቱኝ ሕዝቦች ፊት ስሜ እንዳይነቀፍ ይህን ሁሉ አላደረግሁም።


ይህንንም ውሳኔ ያደረግኹበት ምክንያት ልባቸው ወደ ጣዖቶቻቸው በማምራት ሕጌንና ሥርዓቴን ስላፈረሱ፥ ሰንበትንም ስላረከሱ ነው።”


“ነገር ግን ልጆቻቸው በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚፈጽመው ሁሉ ሕይወት የሚያስገኝለትን ሕጌን አፈረሱ፤ ሕጎቼንም አልጠበቁም፤ ሰንበትንም አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ሳሉ የቊጣዬን ኀይል በእነርሱ ላይ በማውረድ ሁሉንም ላጠፋቸው አስቤ ነበር።


ይህንንም ያደረግኹት ሕጌን ስለ ተላለፉ፥ ሥርዓቴንም ስላልተከተሉ፥ ሰንበትን ስላረከሱ፥ የቀድሞ አባቶቻቸውንም ጣዖቶች ስለ አመለኩ ነው።


በግብጽ በረሓ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ፈረድኩ በእናንተም ላይ እፈርዳለሁ፤” ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።


ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።


ለእኔ የተቀደሱ በሆኑ ነገሮች ላይ አክብሮት የላችሁም፤ ሰንበቴንም አረከሳችሁ።


እነርሱ የፈጸሙት በደል ይህ ብቻ አይደለም፤ ቤተ መቅደሴንም በዚያን ጊዜ አርክሰዋል፤ ሰንበቴንም ሽረዋል።


እኔ የምሰጣችሁን ኅጎቼንና ሥርዓቴን ጠብቁ፤ ይህን በማድረግ ማናቸውም ሰው ሕይወቱን ያድናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”


ትእዛዞቼን ባትጠብቁ፥ ሕግጋቴን ብትንቁ፥ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱና ሥርዓቶቼን ብትጸየፉ፥


ከሕዝብዋ ባዶ የሆነችው ምድር ውድማ ሆና ሰንበቶችን ታከብራለች፤ እነርሱም ሥርዓቴን ስላልተቀበሉና ሕጌን ስላላከበሩ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣቱን በሙሉ ይቀበላሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕጌን ጥሰዋል፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም፤ አባቶቻቸው ይከተሉአቸው የነበሩት የሐሰት አማልክት እነርሱንም አስተዋቸዋል፤


ከእነዚህ ሕዝብ አንዱም ወደዚያች ምድር ለመግባት በሕይወት አይኖርም፤ በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግኋቸውን ተአምራት ሁሉ አይተዋል፤ ነገር ግን የትዕግሥቴን ብዛት ደጋግመው በመፈታተን ለእኔ መታዘዝ እምቢ አሉ።


ሁላችሁም ትሞታላችሁ፤ ሬሳችሁም በዚህ ምድረ በዳ ተበትኖ ይቀራል፤ በእኔ ላይ በማጒረምረማችሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ከኻያ ዓመት በላይ ዕድሜ ኖሮአችሁ የተቈጠራችሁት ሁሉ ከቶ ወደዚያች ምድር አትገቡም፤


“ከእነዚህ ሰዎች ርቃችሁ ቁሙ፤ እኔ እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ!” ሁለቱም በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፉ፤


ከይሳኮር ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።


ሕግን በመከተል ስለሚገኘው ጽድቅ ሙሴ የጻፈው “ሕግን የሚፈጽም ሁሉ በሕይወት ይኖራል” የሚል ነው።


የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤


“እግዚአብሔር አምላክህን በበረሓ እንዴት እንዳስቈጣኸው ከቶ አትርሳ፤ የግብጽን ምድር ለቀህ ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ እስከ መጣህበት እስከ አሁን ድረስ በእርሱ ላይ ዐምፀሃል።


በሲና በረሓ እንኳ እናንተን ለማጥፋት እስኪነሣሣ ድረስ እግዚአብሔርን በብርቱ አስቈጥታችሁታል።


ስለዚህ ይህን ምክር የሚቃወም፥ የሚቃወመው ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።


እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤


跟着我们:

广告


广告