ሕዝቅኤል 20:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በተሰደድን በሰባተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሕዝብ መሪዎች ጥቂቶቹ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ ሊጠይቁኝ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በሰባተኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶቹ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ሊጠይቁ መጡ፤ በፊቴም ተቀመጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንዲህም ሆነ በሰባተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በአሥረኛው ቀን፥ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ሰዎች ጌታን ሊጠይቁ መጡ፥ በፊቴም ተቀመጡ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንዲህም ሆነ፥ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን እግዚአብሔርን ይጠይቁ ዘንድ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ሰዎች መጡ፤ በፊቴም ተቀመጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እንዲህም ሆነ፥ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔርን ይጠይቁ ዘንድ ከእስራኤል ሽማግሌዎች አያሌ ሰዎች መጡ፥ በፊቴም ተቀመጡ። 参见章节 |