ሕዝቅኤል 18:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 “ነገር ግን ደግ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሰዎች የሚያደርጉአቸውን ክፉና አጸያፊ ነገሮች ማድረግ ቢጀምር፥ በሕይወት መኖር የሚችል ይመስላችኋልን? አይደለም! እንዲያውም ያደረገው የደግነት ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ባለመታመኑና ኃጢአተኛም በመሆኑ ምክንያት ይሞታል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 “ጻድቅ ሰው ግን ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአት ቢሠራ፣ ኀጢአተኛው የሚያደርገውንም አስጸያፊ ነገር ቢፈጽም፤ ይህ ሰው በውኑ በሕይወት ይኖራልን? ከሠራው ጽድቅ አንዱም አይታሰብለትም፤ ታማኝነቱን በማጕደሉና ከፈጸመው ኀጢአት የተነሣ ይሞታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኀጢአትንም ቢሠራ፥ ኀጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ በአደረገው ዐመፅና በሠራት ኀጢአት በዚያች ይሞታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም፥ ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል። 参见章节 |