ሕዝቅኤል 18:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “ ‘ታዲያ ልጁ በአባቱ ኃጢአት ምክንያት ያልተቀጣው ስለምንድን ነው?’ ትሉ ይሆናል፤ ልጁ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር አድርጎአል፤ ሕጌን አክብሮአል፤ ስለዚህ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 “እናንተ ግን፣ ‘ልጅ ስለ አባቱ ኀጢአት ለምን አይቀጣም?’ ትላላችሁ። ልጁ ቀናና ትክክለኛውን ነገር ስላደረገ፣ ሥርዐቴንም ሁሉ በጥንቃቄ ስለ ጠበቀ በሕይወት ይኖራል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እናንተ ግን፦ የአባትን ኃጢአት ልጁ ለምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅና ቢያደርገው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 “እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኀጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን በአደረገ፥ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና በአደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል። 参见章节 |