Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በድኾች ላይ ምንም ዐይነት ግፍ ባይሠራ፥ ገንዘቡን በአራጣ አበድሮ ከፍተኛ ወለድ ባያስከፍል፥ ሕጌን ቢያከብር፥ ሥርዓቴን ቢከተል፥ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አባቱ በሠራው ኃጢአት ምክንያት አይሞትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እጁን ደኻን ከመበደል ቢሰበስብ፣ ዐራጣ ወይም ከፍተኛ ወለድ ባይቀበል፣ ሕጌን ቢጠብቅ፣ ሥርዐቴንም ቢከተል፣ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ድሀ ከመበደል እጁን ቢመልስ፥ አራጣ ወይም ትርፍ ባይወስድ፥ ፍርዴን ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እጁ​ንም ከዐ​መፅ ቢመ​ልስ፥ አራ​ጣ​ንም አት​ርፎ ባይ​ወ​ስድ፥ ፍር​ዴ​ንም ቢያ​ደ​ርግ፥ በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ በአ​ባቱ ኀጢ​አት አይ​ሞ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እጁንም ድሀን ከመበደል ቢመልስ አራጣን ትርፎቻንም ባይወስድ ፍርዴንም ቢያደርግ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 18:17
28 交叉引用  

ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።


በአካሄዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው፥ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት የሚኖሩ ሰዎች የተባረኩ ናቸው።


የማይሳሳቱና በእግዚአብሔር መንገድ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።


ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።


አንድ ንጉሥ ለድኾች በቅን የሚፈርድ ከሆነ ለረዥም ዘመን ያስተዳድራል።


ደግ ሰው ስለ ድኾች መብት ይቈረቈራል፤ ክፉ ሰው ግን ለእንደዚህ ዐይነቱ ነገር ግድ አይኖረውም።


እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤


ለድኾች በቅንነት ስለሚፈርድ፥ ሁሉ ነገር ይሳካለት ነበር፤ እግዚአብሔርን ማወቅ ይሉሃል ይህ ነው።


ገንዘቡን በአራጣ ቢያበድርና ከፍተኛ ወለድ ቢያስከፍል፥ ታዲያ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ሊኖር ይችላልን? ከቶ በሕይወት ሊኖር አይችልም፤ ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር በማድረጉ በእርግጥ ይሞታል፤ ለሞቱም ተጠያቂው እርሱ ራሱ ይሆናል።


አባቱ ግን ብዝበዛን ስለ ፈጸመ፥ ወንድሙን ስለ ቀማና በሕዝቡ ዘንድ መልካም ያልሆነውን ነገር ስላደረገ በበደሉ ይሞታል።


የሚያደርገው ነገር ከንቱ መሆኑን ተገንዝቦ ኃጢአት መሥራቱን ስለ ተወ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤


ለልጆቻቸውም እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ባወጡት ድንጋጌ አትመሩ፤ ሥርዓታቸውንም አትከተሉ፤ ወይም በጣዖቶቻቸው አትርከሱ፤


አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እንደ አባቶቻችሁ ራሳችሁን በማርከስና የእነርሱን አጸያፊ ጣዖቶች በማምለክ ለምን ትስታላችሁ?


በደግነቱ የታወቀ ጻድቅ ሰው ኃጢአት ከመሥራት እንዲገታ ብታስጠነቅቀውና የአንተን ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ኃጢአት ከመሥራት ቢቈጠብ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም በኀላፊነት ከመጠየቅ ራስህን ታድናለህ።”


ጻድቅ ሰው በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለውም እርሱ ግን ‘የቀድሞ የጽድቅ ሥራዬ ይበቃኛል’ ብሎ ኃጢአት መሥራት ቢጀምር፥ ከቀድሞ መልካም ሥራው አንዱንም እንኳ አላስታውስለትም፤ ስለዚህም በኃጢአቱ ምክንያት ይሞታል።


ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።”


ትእዛዞቼንና ኅጎቼን ጠብቁ፤ ከእነዚህ ርኲሰቶች እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳን አንዳቸውንም አታድርጉ።


“እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽሙ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ይፈጽሙት የነበረውን የረከሰ ልማድ አትከተሉ፤ ከእነዚህ አሳፋሪ ተግባሮች አንዱንም በመፈጸም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”


ኅጎቼን ፈጽሙ፤ ሥርዓቴን ጠብቁ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


ከቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሕጌ ርቃችኋል፤ አልጠበቃችሁትምም። ‘ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’፥ እናንተ ግን ‘ወደ አንተ የምንመለሰው በምን ዐይነት ነው?’ ትላላችሁ።


ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”


በመልካም ሥራ በመጽናት ምስጋናና ክብርን የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚፈልጉ እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል።


跟着我们:

广告


广告