Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 18:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አባቱ ከእነዚህ በደሎች አንዱን እንኳ የፈጸመ ባይሆን፥ ልጁ ግን በተራራ በጣዖት ቦታዎች የታረደውን ቢበላ፥ የሰውን ሚስት ቢደፍር፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አባትየው አንዱንም ባያደርግ፣ “ልጁ ግን በኰረብታ መስገጃ የቀረበውን ቢበላ፣ የባልንጀራውን ሚስት ቢያባልግ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱም እነዚህን ሁሉ ባይሠራ፥ በተራራም ላይ ቢበላ፥ የባልንጀራውን ሚስት ቢያረክስ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም በጻ​ድቅ አባቱ መን​ገድ ባይ​ሄድ፥ በተ​ራ​ራም ላይ ቢበላ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ቢያ​ረ​ክስ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም ጻድቅ አባቱ የሠራውን ሁሉ ባይሠራ በተራራም ላይ ቢበላ የባልንጀራውንም ሚስት ቢያረክስ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 18:11
15 交叉引用  

ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዐይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተሰብህ መቃብር አይቀበርም።’ ”


የእግዚአብሔር ነቢይ ግን “የሀብትህን እኩሌታ ብትሰጠኝ እንኳ ወደ ቤትህ አልሄድም፤ ከአንተ ጋር እህል ውሃም አልቀምስም።


“ነገር ግን ይህ ሰው ዐመፀኛና ነፍሰ ገዳይ የሆነ፥ ከእነዚህም ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ልጅ ቢኖረው፥


ለእስራኤላውያን ጣዖቶች ባይሰግድ፥ ወይም በተከለከሉ መስገጃዎች የተሠዋውን ማንኛውንም ነገር ባይመገብ፥ የሌላ ሰው ሚስት ባይደፍር፥


አንዳንዶቹ ከጐረቤቶቻቸው ሚስቶች ጋር ያመነዝራሉ፤ ሌሎችም ምራቶቻቸውን ይደፍራሉ፤ እንዲሁም ከአባት የተወለዱትን እኅቶቻቸውን ያረክሳሉ፤


ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው፤” አላት።


ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ።


እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።


ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፥ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ሁሉ አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።


ከመልካም ሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።


የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምንፈጽምና እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም የምናደርግ ስለ ሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告