Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚያም በኋላ ከእስራኤል ምድር ዘር ወስዶ በቂ ውሃ እያገኘ በሚያድግበት በአንድ ለም ስፍራ ተከለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘ከዚህ በኋላ ከምድሪቱ ዘር ወስዶ በመልካም ዐፈር አኖረው፤ ውሃ እንደ ልብ ባለበት ቦታ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ ተከለው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከምድሪቱም ዘር ወሰደ፥ በመልካም መሬትም አኖረው፥ በብዙ ውኃ አጠገብም እንደ አኻያ ዛፍ ተከለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ከም​ድ​ርም ዘር ወሰደ፤ በፍ​ሬ​ያማ እር​ሻም ዘራው፤ በብ​ዙም ውኃ አጠ​ገብ እንደ አኻያ ዛፍ አኖ​ረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከምድርም ዘር ወሰደ በፍሬያማ እርሻ ተከለው በብዙም ውኃ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ አኖረው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:5
12 交叉引用  

ናቡከደነፆር በኢኮንያን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጐት በይሁዳ አነገሠ፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው።


ሕዝቡ የሰበሰቡትን ሀብት እንደ ያዙ የአኻያ ዛፍ የበቀለበትን ሸለቆ ተሻግረው ይሄዳሉ፤


እነርሱ ውሃ በደንብ እንደ ጠጣ ሣር፥ በወራጅ ምንጮች አጠገብ እንዳለ የአኻያ ዛፍ ሁልጊዜ የለመለሙ ይሆናሉ።


አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነርሱም ሥር ሰደዋል፤ አድገውም ፍሬ ያፈራሉ፤ በአፋቸው ያከብሩሃል፤ ልባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን የኢዮአቄም ልጅ በነበረው በኢኮንያን ምትክ በይሁዳ ላይ አነገሠው።


ከንጉሡም ቤተሰብ አንዱን ወስዶ ከእርሱ ጋር የስምምነት ውል አደረገ፤ ለእርሱም ታማኝ እንዲሆንለት በመሐላ ቃል አስገባው፤ ሌሎቹንም የታወቁ ሰዎች ወሰዳቸው።


ተክሉም አደገና ከምድር ብዙ ከፍ ሳይል በሰፊው የተንሰራፋ የወይን ተክል ሆነ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ንስሩ ከፍ ብለው አደጉ፤ ሥሮቹም ወደ መሬት ዘልቀው ገቡ፤ የወይን ተክሉ ብዙ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች አብቅሎ ነበር።


እዚያም ዛፉን የሚያሳድገው በቂ ውሃ ነበረው፤ በመሬት ውስጥ ያለው ጥልቅ ውሃ ዛፉን ያሳድገዋል፤ ጅረቶችም በሜዳ በተተከሉ ዛፎች ዙሪያ ይፈስሳሉ።


ይህም ዛፍ ብዙ ውሃ በማግኘቱ፥ ቁመቱ ከሌሎች ዛፎች ሁሉ የረዘመ ሆነ፤ ቅርንጫፎቹም ወፍራሞችና ረጃጅሞች ሆኑ።


跟着我们:

广告


广告