Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ባቢሎናውያን ብዙ ሰዎችን ለመግደል ቦይ ቆፍረው ዐፈር በመደልደል ምሽግ በሚሠሩበት ጊዜ፥ የግብጽ ንጉሥ ብዙ ተዋጊና ብርቱ ሠራዊት እንኳ መጥቶ በመዋጋት ሊረዳው አይችልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በባቢሎናውያን ብዙ ሕይወት ለማጥፋት በከተማዪቱ ዙሪያ ዐፈር በሚደለድሉበትና ምሽግ በሚሠሩበት ጊዜ፣ ፈርዖን ከኀያል ሰራዊቱና ከብዙ ጭፍሮቹ ጋራ በጦርነት ሊረዳው አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ብዙ ነፍሳትን ለማስወገድ ጉብታ በደለደሉ፥ ቅጥርንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከኃያል ሠራዊቱና ከታላቅ ጉባኤው ጋር በጦርነት አይረዳውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ብዙ​ዎ​ችን ነፍ​ሳት ለማ​ስ​ወ​ገድ ምሽ​ግን በመ​ሸጉ፥ ቅጥ​ር​ንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈር​ዖን በታ​ላቅ ኀይ​ልና በብዙ ሕዝብ በጦ​ር​ነት አይ​ረ​ዳ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ብዙዎችን ነፍሳት ለማስወገድ አፈርን በደለደሉ ምሽግም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከብዙ ሠራዊቱና ከታላቁ ጉባኤው ጋር በሰልፍ አይረዳውም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:17
10 交叉引用  

ምንአልባት ግብጽ ትረዳኛለች ብለህ ተስፋ አድርገህ ይሆናል፤ ነገር ግን በእርስዋ መታመን በሸምበቆ የመደገፍ ያኽል መሆኑን ዕወቀው፤ ተሰንጥሮ እጅህን ከሚወጋው በቀር ሸምበቆ ለምንም አይጠቅምህም፤ በግብጽ ንጉሥ የሚተማመንም የሚገጥመው ዕድል ይህንኑ የመሰለ ነው።’ ”


ከሕዝቡ መካከል ከባቢሎናውያን ጋር በሚዋጉበት ጊዜ ከክፋታቸው የተነሣ እኔ ፊቴን ከዚህች ከተማ ስላዞርኩ በቊጣዬና በመዓቴ በምገድላቸው ሬሳዎች ቤቶቹ የተሞሉ ይሆናሉ።


በዚያን ጊዜ የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከበበ፤ ነገር ግን የግብጽ ሠራዊት ድንበሩን አልፎ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ወደ ኋላው አፈገፈገ።


ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በመምጣት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል አስከበባት፤ ሠራዊቱም በከተማይቱም ዙሪያ ሰፈረ፤ በቅጥሩም ዙሪያ ዐፈር ቈለለ።


በከንቱ ረዳት በመጠበቅ ዐይናችን ደከመ ሊታደግ ከማይችል ሕዝብ በጒጒት ርዳታ ጠበቅን።


ልክ እንደ አንድ ከተማ አስመስለህ በጡቡ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ፤ እስከ ጫፍ ድረስ የዐፈር ቊልልና መወጣጫ ሠርተህ ጡቡን በጠላት ወታደር እንደሚከበብ አስመስለህ ክበባት። በሁሉም አቅጣጫ የእንጨት ምሰሶ ሠርተህ የከተማይቱን የቅጥር በር የምታፈርስ አስመስል።


ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ በአንዲት በተመሸገች ከተማ ላይ ከበባ አድርጎ ይይዛታል፤ የግብጽም ወታደሮች እርሱን መቋቋም ይሳናቸዋል፤ ከእነርሱ ምርጥ የሆኑት እንኳ እርሱን ለመቋቋም በቂ ኀይል አይኖራቸውም።


ፍሬ የማያፈሩትን ሌሎች ዛፎች ግን እየቈረጥህ በመከመር ከተማይቱ እስከምትማረክበት ጊዜ ድረስ ለከበባ ተግባር ልትጠቀምባቸው ትችላለህ።


跟着我们:

广告


广告