Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ዐምፆ ፈረሶችንና ታላቅ ሠራዊት እንዲያመጡለት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ታዲያ ይህ ዕቅዱ ይሳካለታልን? በዚህስ ሊያመልጥ ይችላልን? ውሉን የሚያፈርስ ከሆነ ከቅጣት ከቶ ያመልጣልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ንጉሡ ግን በርሱ ላይ ዐመፀ፤ ፈረሶችና ብዙ ሰራዊት ለማግኘት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ይሳካለት ይሆን? እንዲህ ዐይነቱን ነገር የፈጸመ ያመልጣልን? ውል ያፈረሰስ ሳይቀጣ ይቀራልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ አፍርሶ ያመልጣልን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 17:15
29 交叉引用  

እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።


አምላክ ሆይ! በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው! በቊጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው።


በሐሰት የሚመሰክር ሰው ሳይቀጣ አይቀርም፤ ሐሰት የሚናገር ከቅጣት አያመልጥም።


ከንቱ ቃላት የጦርነት ስልትና ኀይል ይሆናል ብለህ ታስባለህን? ኧረ ለመሆኑ በእኔ ላይ ያመፅከው በማን ተማምነህ ነው?


ንጉሥ ሴዴቅያስም ማምለጫ የለውም፤ እርሱ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፎ ይሰጣል፤ ንጉሡን ፊት ለፊት ያየዋል፤ በግሉም ያነጋግረዋል።


አንተም ማምለጥ አትችልም፤ ትማረካለህ፤ ለእርሱም ተላልፈህ ትሰጣለህ፤ እርሱን በቀጥታ ፊት ለፊት ታየዋለህ፤ እርሱም ያነጋግርሃል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤


ለእነርሱ እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ተላልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ማምለጥ አትችልም።”


በተጨማሪም እንዲህ አልኩት፦ “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ይወሰዳሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ ተይዘህ እስረኛ ትሆናለህ፤ ከእነርሱ እጅ ከቶ አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ተቃጥላ ትወድማለች።”


ስለዚህም እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው። ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤


እርሱ መሐላውን በመናቅ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሰና እጁን ከሰጠ በኋላ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስላደረገ አያመልጥም።”


“እንዲሁም ታላላቅ ክንፎችና ብዙ ላባዎች ያሉት ሌላ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ አሁን እንግዲህ የወይን ተክሉ ሥሮቹንና ቅርንጫፎቹን ወደ ንስሩ ዘረጋ፤ ይህንንም ያደረገው ከተተከለበት መደብ ውሃ ያጠጣው ዘንድ ነው።


“ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ ይህ የተተከለው የወይን ተክል ይጸድቃልን? የመጀመሪያው ንስር ሥሩን ነቅሎ ፍሬው እንዲበሰብስና እንዲደርቅ እንዲሁም ለምለም ቅጠሉ እንዲጠወልግ አያደርገውምን? ሥሩን ለመንቀል ጠንካራ የጦር መሣሪያ ወይም ኀይለኛ ሠራዊት አያስፈልገውም።


“አንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላብህ የእስራኤል መሪ! ለመጨረሻ ጊዜ የምትቀጣበት ቀን እነሆ ቀርቦአል።


“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ ስለ ዐሞናውያንና ስለ ስድባቸው እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን እንዲህ ብለህ አስታውቃቸው፤ ‘አጥፊ ሰይፍ ተዘጋጅቶአል፤ ለመግደልና ለማውደም እንደ መብረቅም ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል!’


ብልቶቻቸው እንደ አህያ፥ ዘራቸውም እንደ አለሌ ፈረስ ሆኖ በፍትወት በሚቃጠሉ ወንዶች ተማረከች።


ይልቁንስ እስራኤል ለእርዳታ ወደ ግብጽ በመሄድ የበደለችውን በደል ታስታውስበታለች እንጂ ርዳታ ለማግኘት ዳግመኛ በእነርሱ ላይ አትተማመንም። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


በእጆቻችሁ በያዙአችሁ ጊዜ ተሰነጣጥቃችሁ ትከሻቸውን ወጋችሁ፤ በእናንተ ላይ በተደገፉ ጊዜ እናንተ ተሰብራችሁ ወገባቸው ተብረከረከ።


እናንተ እባቦች፥ እባብ ልጆች፥ እንዴት ከገሃነም ቅጣት ማምለጥ ትችላላችሁ?


ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ።


ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።


ለእነርሱ የምናደርገው እንደዚህ ነው፦ ለእነርሱ ስለማልንላቸው መሐላ የእግዚአብሔር ቊጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ እንተዋቸው።


跟着我们:

广告


广告