Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የሰጠሽውን የተስፋ ቃል ንቀሽ ቃል ኪዳን በማፍረስሽ የሚገባሽን ቅጣት እሰጥሻለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቃል ኪዳኔን በማፍረስ መሐላዬን ንቀሻልና ተገቢውን ቅጣት ከእኔ ዘንድ ትቀበያለሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ቃል ኪዳንን በማፍረስ መሐላን ንቀሻልና፥ አንቺ እንዳደረግሽ እኔ ደግሞ አደርግብሻለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳ​ንን በማ​ፍ​ረስ መሐ​ላን የና​ቅሽ ሆይ! አንቺ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሽ እኔ ደግሞ አደ​ር​ግ​ብ​ሻ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ አንቺ ቃል ኪዳንን በማፍረስ መሐላን የናቅሽ ሆይ፥ አንቺ እንዳደረግሽ እኔ ደግሞ አደርግብሻለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:59
19 交叉引用  

ሰዎች ሕጎችን በመጣስ፥ ደንብን በመተላለፍና ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በማፍረስ ምድርን አርክሰዋል።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


እኔ ያዘዝኳቸውን ለመፈጸም እምቢ ይሉ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት ይሠራሉ፤ ባዕዳን አማልክትን ያመልካሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ በአንድነት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።


እነሆ የራስሽ ክፋት ይቀጣሻል፤ ክሕደትሽ ይፈርድብሻል፤ እኔን አምላክሽን እግዚአብሔርን መተውሽና ለእኔም የምታሳዪውን ክብር ማስቀረትሽ ምን ያኽል ከባድና መራራ በደል እንደ ሆነ ትረጂአለሽ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ ነኝ።”


እናንተ ከእኔ ከአምላካችሁ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችሁ ባዕዳን አማልክትን በማምለካችሁና በማገልገላችሁ ምክንያት መሆኑንም ይረዳሉ።”


ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ልባቸውን ለጣዖቶች የሰጡና የጣዖት አምልኮአቸው በፊታቸው ዕንቅፋት እንዲሆንባቸው ያደረጉ አሉ፤ እነዚህ ሰዎች ወደ ነቢዩ የሚመጡ ከሆነ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖቶች ብዛት ተገቢ መልስ እሰጣቸዋለሁ።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ በእኔ ስም የማለውን መሐላ ንቆ ቃል ኪዳኑን በማፍረሱ መሐላው በራሱ ላይ እንዲደርስ አደርጋለሁ።


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አሁን መጥፊያችሁ ደርሶአል። ቊጣዬን አወርድባችኋለሁ፤ እንደ አካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ ስለ ርኲሰታችሁም ሁሉ እቀጣችኋለሁ።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም። በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


በዚያን ጊዜ የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ሁሉ ስለምን አደረገ? ለብርቱ ቊጣውስ ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው?’


መልሱም፦ ‘እነርሱ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው።


跟着我们:

广告


广告