Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 “እኔ ሕያው እንደ መሆኔ የምለው ይህ ነው፤ እኅትሽ ሰዶምና መንደሮችዋ አንቺና መንደሮችሽ ካደረጋችሁት የባሰ ክፋት አልሠሩም፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 በሕያውነቴ እምላለሁ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ አንቺና ሴት ልጆችሽ ያደረጋችሁትን እኅትሽ ሰዶምና ልጆቿ እንኳ አላደረጉትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ አንቺና ሴቶች ልጆችሽ እንዳደረጋችሁት ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ አላደረጉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 እኔ ሕያው ነኝ! አን​ቺና ሴቶች ልጆ​ችሽ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት እን​ዲሁ ሰዶ​ምና ሴቶች ልጆ​ችዋ አላ​ደ​ረ​ጉም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 እኔ ሕያው ነኝና አንቺና ሴቶች ልጆችሽ እንዳደረጋችሁት እንዲሁ ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ አላደረጉም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:48
9 交叉引用  

“ታላቅ እኅትሽ ከመንደሮችዋ ጋር በስተ ሰሜን የምትገኘው ሰማርያ ናት፤ ታናሽ እኅትሽም ከመንደሮችዋ ጋር በስተ ደቡብ የምትገኘው ሰዶም ናት፤


የእነርሱን አካሄድ ተከትለሽ አጸያፊ ሥራቸውን መሥራትሽ ብቻ ሳይሆን በአካሄድሽ ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእነርሱ የበለጠ ጥፋት ሠራሽ።


እነሆ አሁንም ውርደትሽን ተሸከሚ፤ የአንቺ ኃጢአት እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሣ እኅቶችሽ ከአንቺ ጋር ሲነጻጸሩ ምንም በደል የሌለባቸው ንጹሖች መስለው ይታያሉ፤ አሁንም እኅቶችሽን በደል የሌለባቸው ንጹሖች እንዲመስሉ በማድረግሽ ኀፍረትን እንደ ልብስ ተከናንበሽ ተቀመጪ።”


ኢየሩሳሌም ግን ሕጎቼንና ደንቤን በመጣስ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የከፋችና በዙሪያዋም ካሉት አገሮች ይበልጥ እምቢተኛ መሆንዋን አሳይታለች፤ ኢየሩሳሌም ሕጎቼንና ደንቦቼን ንቃለች፤ ትእዛዞቼንም አልተከተለችም።”


በእውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ሰዎች ቅጣቱ ይቀልላቸዋል።


ሰዎች በማይቀበሉአችሁና በማይሰሙአችሁ ቦታ ሁሉ የእግራችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ፤ ይህም ለእነርሱ የማስጠንቀቂያ ምስክር ይሆንባቸዋል።”


በፍርድ ቀን ከዚህች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ከተማ ቅጣቱ ይቀልላታል እላችኋለሁ።”


ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? እነርሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ በመስጠት ገደላችሁት።


跟着我们:

广告


广告