ሕዝቅኤል 16:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 በዚህ ምክንያት ከእነርሱ ጋር የተደሰትሽባቸውን ማለት የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ ተጋልጠሽ ዕርቃንሽን ያዩ ዘንድ ከአካባቢው ሰብስቤ አንቺን በፊታቸው አራቊትሻለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም37 በዚህ ምክንያት ደስ የተሠኘሽባቸውን ወዳጆችሽን፣ የወደድሻቸውንና የጠላሻቸውን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከየአቅጣጫው ሁሉ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፤ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ፤ እነርሱም ኀፍረተ ሥጋሽን ሁሉ ያያሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 ስለዚህ እነሆ እኔ ከአንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ የምትወጃቸውንም ከምትጠያቸው ጋር በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ ይከቡሻል፤ በእነርሱም ዘንድ ጕስቍልናሽን እገልጥብሻለሁ፤ ሁሉም ኀፍረትሽን ያዩብሻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽ ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፥ በአንቺ ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፥ ኅፍረተ ሥጋሽንም ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ። 参见章节 |